ቱአሬጎች ከሊቢያው ጦርነት በኋላ | አፍሪቃ | DW | 14.03.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ቱአሬጎች ከሊቢያው ጦርነት በኋላ

የቱአሬግ አርብቶ አደሮች ‘አዛዋድ’ብለው በሚጠሩት የሰሜን ማሊው በረሃ በመንግሥት ወታደሮችና በቱአሪግ አማጽያን መካከል ከጥር መጀመሪያ አንስቶ የተኩስ ልውውጥ እና የአየር ድብደባም እየተካሄደ ነው ። ሰለ ውጊያው የሚወጡ ዘገባዎችየቱአሬግ አርብቶ አደሮች ‘አዛዋድ’ብለው  በሚጠሩት የሰሜን ማሊው በረሃ  በመንግሥት ወታደሮችና በቱአሪግ አማጽያን መካከል ከጥር መጀመሪያ አንስቶ የተኩስ ልውውጥ እና  የአየር ድብደባም እየተካሄደ ነው ። ሰለ ውጊያው የሚወጡ  ዘገባዎች ግን በርሰ በርስ የሚጋጩ  ናቸው ። ስለ ሞቱና የቆሰሉ ሰዎች ቁጥር አስተማማኝ መረጃ የለም  ። ይሁንና ከ120,000በላይ ሰዎች ከአካባቢያቸው ተሰደው ወደ ተባበሩት መንግሥታት መጠለያዎች ሸሽተዋል ። ጉዳዩን በቀርብ የሚያውቁ ተንታኞች እንደሚሉት ውጊያው የሊቢያው ጦርነት መዘዝ ነው ። የዶቼቬለዋ Julia Hahn የዘገበችውን ሂሩት መለሠ አጠናቅራዋለች ።
እጅግ የደየኽየውና አስቸጋሪው ሰሜን ማሊ የሚገኘው በረሃ  የቆዳ ስፋቱ ከፈረንሳይ ጋር ይስተካከላል ። በዚህ አካባቢ ከሳምንታት አንስቶ የማሊ ጦርና የአዛዋድ በሔራዊ የነፃነት ንቅናቄ በእንግሊዘኛው ምህፃር MNLA በመባል የሚጠራው አዲሱ የአማፅያን ቡድን እየተዋጉ ነው ። በ ጀርመኑ የ Bayreuth ዩኒቨርስቲ የማሊ ጉዳዮች አጥኚ Georg Klute እንደሚሉት የአሁኑ ውጊያ የሊቢያው ጦርነት መዘዝ ነው  ።
« ከባዱ ውጊያ ፣የሊቢያው ጦርነትና የሰሜን አትላንቲክ የጋራ መከላከያ ቃል ኪዳን ድርጅት በምህፃሩ NATO የሊቢያ ዘመቻ  ወጤት ነው ። ምክንያቱም በሊቢያ አገዛዝ ልዩ ልዩ ክፍሎች ውስጥ ይሠሩ የነበሩ በርካታ ወታደሮች ወደ ደቡብ ተሰደዋልና ። »


በመገናኛ ብዙሃን ዘገባ መሠረት ቁጥራቸው እስከ 4000 የሚደርስ የቱአሬግ ቅጥርኛ ተዋጊዎች ከሊቢያ በተለይም ወደ ኒዠር ና ማሊ  ገብተዋል ። አበዛኛዎቹ በሊቢያው ህዝባዊ አብዮት ወቀት ለጋዳፊ ጦር ተሰልፈው ተዋግተዋል ። ቅጥረኞቹ የማሊን ድንበር አቋርጠው ጥር መጀመሪያ ላይ ሮኬቶች ና ሌሎች በቀላሉ የሚንቀሳቀሱ የጦር መሣሪያዎችን በሻንጣቸው ሸክፈው ነው ማሊ የገቡት ።
« እነዚህ የጦር መሣሪያዎች የጋዳፊ ጦር መሆናቸው ፍፁም ግልፅ  ነው ። የጦር መሣሪያዎቹ የማሊ ጦር ከታጠቃቸው መሣሪያዎች  እጅግ በጣም የተሻሉ ናቸው ። በአማፅያን ዘንድ ያለው አዲሱ ነገር ይሄ ነው ። »
ይላሉ በፍራንክፈርት ዩኒቨርስቲ የሰነ ሰበ ምሁር  የማሊው ተወላጅ ማማዱ ዲያዋራ ።
MNLA ራሱን  ፣ የአብዮታዊ ንቅናቄ ቡድን ፣ የቱአሬጎች ድምፅ አድርጎ የሚቆጥረው  ። ከዚህ በተጨማሪም አረቦችን ማውሮችንና ፉላኒዎችንም ደጋፊዎቼ  ናቸው ነው የሚለው ። ግቡ አዝዋድ የምትባል ነፃ ሃገር መመሥረት  ነው ።ሙሳ አግ አሳሪ የአማፅያኑ ቃል አቀባይ ናቸው ። ከመንግሥት ጋር የሚካሄደው ድርድር ያልሰመረበትን ምክንያት ያስረዳሉ
« በሰላማዊ ፣ዴሞክራሲያዊ መንገዶች ሞክረናል ። ሆኖም መፈናፈን የማንችልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው ።  አዎ መደራደር እንፈልጋለን ። ይሁንና እንዳለመታደል ሆኖ መንግሥት መልስ የሚሰጠን በጦር እርምጃ ነው ። »

Libyen Sahara Tuaregs


የቱአሬጎች ትግል  እድሜ ማሊ ነፃነትዋን ካወጀችበት ጊዜ ጋር ይስተካከላል  ። በማሊና በሌሎቹም የሳህል ሃገራት አናሳ የሆኑት  አርብቶ አደር የህብረተሰብ  ክፍሎች በመንግሥት ውስጥ ውክልና የለንም የሚል ስሜት ነው ያላቸው  ።  እጎአ ከ 1960 አንስቶ በተለይም ማሊና ቻድ የሚገኙት አርብቶ አደሮች በየጊዜው እንዳመፁ ነው ። እጎአ ከ 2005 እስከ 2009 ዓም የተካሄደው የቅርብ ጊዜው  አመፅ ነው ። እነዚህን ግጭቶች ለማስቆም የተካሄዱት ድርድሮች ከሽፈዋል ። ለማሊው ፐሬዝዳንት የሃገሪቱ መከፈል ጥያቄ ውስጥ የሚገባ ጉዳይ አይደለም ።  በሚያዚያ አጋማሽ አካባቢ ምርጫ ይካሄዳል ። እስከዚያ ድረስ የማሊ ጦር አማፅያኑን ድል ማድረግ ነወ ፍላጎቱ ። የማሊ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱሜሊያ ቦቤዬ ማይጋ ፣ መንግሥት የደኽየውን ሰሜናዊ የሃገሪቱ ክፍል ኤኮኖሚ ለማልማት  ፣ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰሱን አፅንኦት ሰጥተው ይናገራሉ ።  ያም ሆኖ ግን ስህተት  መኖሩንም ያምናሉ ።

Tuareg mit blauem Turban


« እርግጥ ነው መንግሥት እዚያ በቅርበት የለም ።ይህም  በተለያዩ ምክንያቶች ለዓመታት ዘልቋል  ። መንግሥት ይህን ግዛት መቆጣጠር እንዳይችል የሚንቀሳቀሱ በርካታ ቡድኖች አሉ ። »
መነገሥት አካባቢውን ሙሉ ለሙሉ ባለመቆጣጠሩ ምክንያት ተጠቃሚ የሆነው MNLA ብቻ አይደለም ። አስቸጋሪው ሰሜን ማሊ ከረዠም ጊዜ አንስቶ የአደንዛዥ ዕፅ አዘዋዋሪዎች ፣ የአክራሪ ሳላፊስቶችና በመግሬብ የአልቃይዳ አባላት መነኻሪያ ሆኗል ። በመግሬብ የአልቃይዳ  ቡድን ባለፉት ጊዜያት አገር ጎብኝዎችን  በማገት ይታውቃል  ። የቱኣሬግ አማፅያን ከዚህ  ቡድን ጋር ግንኙነት አላቸው ተብሎ  ይጠረጠራል ። ይሁንና ደያዋራ እንደሚሉት ለዚህ ማረጋገጫ የለም ።

ሂሩት መለሠ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 14.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14HrP

ተዛማጅ ዘገባዎች

 • ቀን 14.03.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/14HrP