ቱኒዚያ፣ ግብፅና የሀሳብ ነፃነት መገደቡ | አፍሪቃ | DW | 08.04.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ቱኒዚያ፣ ግብፅና የሀሳብ ነፃነት መገደቡ

በቱኒዚያ እና ግብፅ ሀሳብን በነፃነት መግለፅ አሁንም አዳጋች እንደሆነ የመብት ተሟጋቾች ይገልፃሉ። ተሟጋቾቹ እንደሚሉት በሁለቱም ሀገራት ከተካሄደው ህዝባዊ አብዮት በኋላ ሀሳብን በነፃነት የመግለፁ ሁኔታ እንቅፋት አላጣውም። አርቲስቶች ፣ የኢንተርኔት አምደኞች እና ጋዜጠኞች እየተከሰሱ ነው። የመብት ተከራካሪዎቹ ይህንን ይቃወማሉ።

Cute Ukrainian woman with blue yellow band on the mouth isolated on a gray background. Sergii Figurnyi - Fotolia

Ukraine Symbolbild gegen Zensur und für Meinungsfreiheit

ግብፃዊው ባሳም ዩሲፍ የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን ሲያቀርብ ማስታወሻ ወረቀት እንኳን በእጁ አይዝም።  በምህፀታዊ ንግግሩ ስለ ፕሬዘደንት ሞሀመድ ሙርሲ የእንግሊዘኛ አነጋገር ይቀልዳል። ፕሬዚዳንቱን « ሱፕር ሙርሲ» እያለም ይጠራቸዋል። ይኼው የመድረክ ሰው ከቅርብ ጊዜ አንስቶ ለዚህ ድርጊቱ ፍርድ ቤት ቀርቧል። አቃቢ ህጉም የፕሬዚዳንቱን እና የእስልምናን እምነት ስም አጥፍቷል ሲል ክስ መስርቶበታል። የዩሲፍ እጣ በቱኒዚያ እና ግብፅ ያሉ በርካታ አርቲስቶች፣ የኢንተርኔት አምደኞች፣ ጋዜጠኞችን እና የፖለቲካ ተቃዋሚዎችንም ገጥሟቸዋል። የተወገደው የአምባገነን ስርዓት ዘላቂ ነፃነት ሲያስገኝ አልታየም።  እንደ ሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች ገለፃ ሀሳብን በነፃነት የመግለፁ ሂደት ዳግም ሲታገድ ይስተዋላል ። ከሰብዓዊ መብት ተማጋቹ ድርጅት አምንስቲ ኢንተርናሽናል የግብፅ ተጠሪ ዲያና ኤልታሃም፤

Egyptian satirist and television host Bassem Youssef is surrounded by his supporters upon his arrival at the public prosecutor's office in the high court in Cairo, on March 31, 2013. Egypt's public prosecutor ordered the arrest of popular satirist Youssef over alleged insults to Islam and to President Mohamed Morsi, in the latest clampdown on critical media. AFP PHOTO / KHALED DESOUKI (Photo credit should read KHALED DESOUKI/AFP/Getty Images)

ግብፃዊው ባሳም ዩሲፍ

« እንደ አምንስቲ ኢንተርናሽናል በጣም የሚያሳስበን ሀሳብን በነፃ በመግለፅ ላይ በቅርቡ የሚደረገው ጫና ነው። ባለፉት ሁለት ሳምንታት እንደተመለከትነው በርካታ ግለሰቦች በግብፅ ባለስልጣናት ተጠርጥረዋል። ይህም በመንግስት የሰብዓዊ ሁኔታ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ያላቸውን አመለካከት በመግለፃቸው ነው።»

አዲሱ የግብፅ ህገ መንግስት ሀሳብን በነፃ መግለፅን ያረጋግጣል። ይሁንና የስም ማጥፋት ወንጀል በቀጥታ ለእስር ይዳርጋል። ምክንያታዊ እና ሞራላዊ ወቀሳዎችን የመንግስት ባለስልጣናት አጥብቀው ይቃወማሉ። የሀይማኖት አባቶች እና የእስልምና ዕምነት ስም ጠፍቷል ሲሉም ብዙ የሲቪሉ ማህበረሰብ እና የሙስሊም ጠበቃዎች ይወቅሳሉ። ።ይሁንና ጉዳዩን በፍርድ ቤት መመልከት የአቃቢ ህጉ ሀላፊነት ነው ይላሉ ኤልታሃም።

በቱኒዚያ ደግሞ በአሁኑ ሰዓት የሚያነጋግረው የአርቲስት አባ ያኮቢ ጉዳይ ነው። አላ ያኮቢ «ፖሊሶች ውሾች ናቸው» በሚል ርዕስ ኢንተርኔት ላይ የጫነው በምስል የታቀፈ ቪዲዮ ምን ያህል ፀጥታ አስከባሪዎች ምን ያህል አስከፊ የሃይል ርምጃ እንደሚወስዱ ያንፀባርቃል።

በመጋቢት አጋማሽ ቪዲዮው ላይ ያሉት ሁለት ዳንሰኞች በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሲውሉም አርቲስቱ የገባበት አይታወቅም። ይሁንና አላ ያኮቢ በሌለበት የሁለት አመት እስራት ተበይኖበታል።

Photographers hold up placards as they protest against government policies and the Muslim Brotherhood's treatment towards photographers, in Cairo March 19, 2013. REUTERS/Khaled Elfiqi/Egyptian Photo Journalistic Society/Pool (EGYPT - Tags: POLITICS MEDIA CIVIL UNREST)

የተቃውሞ ሰልፍ በካይሮ

በከፊል እየታየ ያለው የክስ ሂደት ለሌሎች ማስፈራሪያ ሆኗል። የግብፃዊው ዩሲፍ  የስም ማጥፋትን የክስ ሂደት ፤ ከአርቲስቱ አልፎ የቴሌቪዥን ጣቢያው ፍቃድን የጣሰ ነው በሚል፤ በአጠቃላይ የቴሌቪዥን ጣቢያው እንዲዘጋ ክስ አስነስቷል።

ኤልታሃም ለተከሳሾች በተለያዩ አካላት ድጋፍ እየተደረገላቸው ይገኛል ይላሉ።

« በተለያዩ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ ጋዜጠኞች የግል ጣቢያዎች ምናልባትም አይታችሁ ከሆነ በርካታ ክስ የተመሰረተባቸው ግለሰቦች ድጋፍ የሚያደርጉላቸው አሉ። የተቃውሞ ሰልፎች ይካሄዳሉ። ቀልደኛ አሊ አንጊል ትናንት ፍርድ ቤት ሲቀርብ ተመሳሳይ ሁኔታ ነው የታየው። ብዙ ደጋፊዎች ተገኝተው ነበር። እንደሚመስለኝ በአካባቢው በርካታ መነቃቃት እና ተቃውሞ ይታያል።»

የዮናይትድ እስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም  ጉዳዩ እንዳሳሰበው ገልጽዋል።  የህክምና ትምህርት ያጠናው ዩሲፍ በራሱ መንገድ ትግሉን ቀጥሏል። ይሁንና በአሁኑ ሰዓት በዋስ ተለቋል።

አንድሪያስ ጎርዘፍስኪ

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic