ቱኒዚያ ከሽብር ጥቃት ማግሥት | አፍሪቃ | DW | 26.11.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ቱኒዚያ ከሽብር ጥቃት ማግሥት

የቱኒዚያ ባለስልጣናት ከትናንት በስተያ ለ12 ሰዎች ህልፈተ ህይወት ምክንያት ከሆነዉ የሽብር ጥቃት ጋር በተገናኘ የሚጠረጠሩ ሰዎችን ማሰር ጀመሩ። በዛሬዉ ዕለት ከተያዙት መካከልም በሕግ የታገደለዉ አንሳር አልሻሪያ የተሰኘዉ ፅንፈኛ ቡድን የቀድሞ ቃል አቀባይ የነበረዉ ግለሰብ አንዱ መሆኑን ዘገባዎች ያመለክታሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:17
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:17 ደቂቃ

ቱኒዚያ ከሽብር ጥቃት ማግሥት

የሀገሪቱ ብሔራዊ ራዲዮ እንደዘገበዉም ግለሰቦ ከቤቱ ተወስዶ ምርመራ እየተካሄደ ነዉ። ሰይፈዲን ራይስ በተደጋጋሚ ከዚህ ወደምም አመፅ በማነሳሳት ክስ በተለያዩ ጊዜያት መታሠሩም ተገልጿል። የፕሬዝደንቱን አንጋቾች በያዘዉ አዉቶቡስ ላይ ማክሰኞ ዕለት ለደረሰዉ ጥቃትም ትናንት ራሱን «እስላማዊ መንግሥት» የሚለዉ ፅንፈኛ ቡድን ኃላፊነት መዉሰዱ ይፋ ሆኗል። ድርጊቱ ያስቆጣቸዉ ቱኒዚያዉያን በአሸባሪዎች ጥቃት እንደማይሸማቀቁ እየገለፁ ነዉ።

ማክሰኞ ዕለት ቱኒዚያ ዉስጥ የደረሰዉ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት በያዝነዉ ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 2015 ሀገሪቱ ዉስጥ ከደረሱት ከባድ ጥቃቶች ለሶስተኛ ጊዜ የተፈፀመ ነዉ። ባለፈዉ መጋቢት ወር የዉጭ ሀገር ዜጎች ጉብኝት በሚያካሂዱበት ቤተ መዘክር፤ እንዲሁም በባህር ዳርቻ መዝናኛ ስፍራም በተፈፀመ ጥቃት 60 ሰዎች ተገድለዋል። ዘገባዎች እንደሚመለክቱት ሶርያ ዉስጥ በሚካሄደዉ የእርስ በርስ ጦርነት ከሚሳተፉ የዉጭ ኃይሎች ከቱኒዚያ የሄዱት በቁጥር ከፍተኛዉ ድርሻ ይይዛሉ። እንደባለስልጣናት ግምት ሶርያ ዉስጥ ለዉጊያ የተሰለፉት ቱኒዚያዉያን 3,000 ይገመታሉ። የዶቼ ቬለዋ ሳራ ሜርሽ ከቱኒዝ የላከችዉን ዘገባ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል እንደሚከተለዉ አጠናቅሮታል።

ይልማ ኃይለሚካኤል

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic