1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱርክ የአውሮፓ ኅብረትና የሶርያ የተኩስ አቁም ሀሳብ

ሰኞ፣ የካቲት 7 2008

በሶርያ በአንድ ሳምንት ጊዜ ዉስጥ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በተለይ ዩኤስ አሜሪካና ሩስያ ከስምምነት ላይ ደርሰዋል ቢባልም ጦርነቱ ግን እንደዉም እየሰፋ እንዳይሄድ ስጋት ፈጥሮአል።

https://p.dw.com/p/1Hvlv
Syrien Verkäufer im zerstörten Aleppo
ምስል Reuters/A. Ismail

[No title]

የፕሬዚዳንት አሳድ ወታደሮች በሩስያ ጦር አዉሮፕላኖች የታገዙ በርካታ አካባቢዎችን መቆጣጠራቸዉና በጦርነቱ የበላይነትን መያዛቸዉ እየተነገረ ነዉ። ትልቋ የሶርያ ከተማ የሆነችዉና በአማፅያን ተይዛ የቆየችዉን የአሌፖ ከተማን ለመቆጣጠር በሚያስችል ሁኔታ የአሳድ ወታደሮች ከተማዋን እንደከበቡ እየተነገረ ባለበት ሁኔታ ነበር ባለፈዉ ሃሙስ ዩኤስ አሜሪካና ሩስያ የሶርያ ተፋላሚ ወገኖች ተኩስ አቁመዉ ወደ ሰላም ድርድር እንዲመጡ መስማማታቸዉ የተገለፀዉ። ይሁን እንጂ ቱርክ ባለፉት ሁለት ቀናት በሶርያ «IS»ን ከሚዋጉት ኃይሎች ጋር አብሮ በመዋጋት የሚታወቀዉን « YPG» የተሰኘዉን የኩርድ ሕዝባዊ ጦር በመድፍ በመደብደብ በሰሜን ምስራቅ ሶርያ የተቆጣጠሩዋትን አካባቢ እንዲለቁ ጠይቃለች። ዝርዝሩን የብራስልሱ ወኪላችን ልኮልናል።


ገበያዉ ንጉሴ


አዜብ ታደሰ
ኂሩት መለሰ