ቱርክ፣ የአውሮጳ ህብረት እና የሶርያ ስደተኞች | ዓለም | DW | 06.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ቱርክ፣ የአውሮጳ ህብረት እና የሶርያ ስደተኞች

የቱርክ ፕሬዚደንት ሬቼፕ ጠይፕ ኤርዶኻን ትናንት በብራስልስ ባደረጉት ይፋ ጉብኝት ከአውሮጳ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ተገናኝተው ወደ ህብረቱ አባል ሃገራት በብዛት ስለሚመጡት ስደተኞች ጉዳይ መከሩ።

ህብረቱ በተለይ የሶርያን ስደተኞች መተላለፊያ ያደረጉዋት ቱርክ የስደተኞቹን ፍልሰት በማከላከሉ ረገድ እንድትተባበር ይፈልጋል። ወደ ሁለት ሚልዮን የሚጠጉ የሶርያ ስደተኞችን የምታስተናግደው ቱርክ በበኩሏ ከህብረቱ የፋይናንስ ድጋፍ፣ ለዜጎችዋ የቪዛ መላላትን የመሳሰሉ በርካታ ጥያቄዎች አቅርባለች። ስለ ቱርክ ፕሬዚደንት ኤርዶኻን እና ስለህብረቱ ባለስልጣናት ውይይት የብራስልሱ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ ይህን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic