ቱርክ፥ የሶርያ ድንበር ላይ አውሮፕላን ተኩሳ ጣለች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 23.03.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ቱርክ፥ የሶርያ ድንበር ላይ አውሮፕላን ተኩሳ ጣለች

የቱርክ የጦር ጄት በሶርያ ድንበር አኳያ አንድ የፕሬዚዳንት ኧል አሳድ ጦር ጄትን ተኩሶ እንደጣለ ተገለፀ።

የሶሪያ የጦርጄትተመቶ የወደቀው የቱርክን የበረራ ክልል ጥሶ በመግባቱ እንደሆነ የቱርክ ርዕሠ-ብሔር ሬሴፕ ታዪፕ ኤርዶዋን አስታውቀዋል። እንደሶሪያ የጦር ሠራዊት መግለጫ ከሆነ ደግሞ የጦር ጄቱ የተተኮሰበት የሶርያ ድንበር ውስጥ እንዳለ ነው። መቀመጫውን ለንደን ውስጥ ያደረገው የሶሪያ ጉዳይ ተመልካች የሰብዓዊ መብት ተቋም የጦር ጄቱ የፕሬዚዳንት ኧል አሳድ መንግስትን በመቃወም ነፍጥ ያነሱ አማፂያን መንግስትን ወደእሚፋለሙበት ላታኪያ የተሰኘ አውራጃ ለመግባት የድንበ ርኬላን ሳይጥስ እንዳልቀረ ጠቅሷል። የቱርኩ ፕሬዙዳንት ኤርዶዋን በሰሜን ምዕራብ ቱርክ ኮቻሊ አውራጃ የጦር ጄቱ ተሞቶ መውደቁን አረጋግጠዋል። የጦር ኃይሉንም ለተሳትፎው ስኬት አመስግነዋል። ኤርዶዋን « በቱርክ የበረራ ክልል ውስጥ ተገኝቶ ሕግ የሚጥስ የሚገባውን አፀፋ ያገኛል» በማለት ለተሰበሰበው የፓርቲያቸው አባላትገልፀዋል። ሶስትአመት ባለፈው የሶርያ የርስ በዕርስ ጦርነት ሳቢያ በሶርያ እና በቱርክ ድንበር ባለፉት ጊዚያት በተደጋጋሚ ግጭቶች ተስተውለዋል። እኢአ ጥቅምት 2012 የቱርክ ድንበር አቅራቢያ ይበር የነበረ አንድ የሶርያ ሂሊኮፕተር ተመቶ መውደቁ ይታወሳል።

ልደትአበበ

ማንተጋፍቶት ስለሺ