ቱርክ እና ተመላሽ ስደተኞች | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 04.04.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ቱርክ እና ተመላሽ ስደተኞች

ስደተኞች ወደ አውሮጳ በሕገ ወጥ መንገድ እንዳይገቡ ለመቆጣጠር የአውሮጳ ህብረት ባለፈው ወር ከቱርክ ጋር የደረሰው ስምምነት ዛሬ ተግባራዊ መሆን ጀመረ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:48
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:48 ደቂቃ

አከራካሪው የአውሮጳ ህብረትና የቱርክ ስምምነት

በዚሁ ስምምነት መሰረትም፣ ከሁለት የግሪክ ደሴቶች ወደ 200 የሚጠጉ ሕገ ወጥ ስደተኞች በዛሬው ዕለት ወደ ቱርክ በግዳጅ እንዲመለሱ ተደርጓል። ይሁንና፣ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች በሰብዓዊ መብት ረገጣ የሚወቅሷት እና አዘውትራም የአሸባሪዎች ጥቃት ሰለባ የሆነችው ቱርክ ለተመላሾች ስደተኞች ዋስትና መስጠት መቻሏ አጠራጣሪ ነው በሚል በስምምነቱ አኳያ አሁንም ቅሬታቸውን እያሰሙ ነው።

ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic