ቱርክ ስደተኞችን በመልቀቅ አዉሮጳን እያስፈራራች ነዉ | ዓለም | DW | 03.03.2020
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ዓለም

ቱርክ ስደተኞችን በመልቀቅ አዉሮጳን እያስፈራራች ነዉ

በሚቀጥሉት ቀናት ከቱርክ በኩል በርካታ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ሕብረት ድንበር እንደሚጎርፍ «ፍሮንቴክክስ » የተባለዉ የአውሮጳ የድንበርና የደሴቶች ተቆጣጣሪ ድርጅት አስጠነቀቀ። «ዲ ቬልት የተሰኘዉ» የጀርመን ዕለታዊ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ከሆነ ከቱርክ በኩል የሚፈልሰው ከፍተኛ ቁጥር ስደተኛ አውሮጳዊትዋ ሀገር ግሪክ  የሚገባ ነው።

በሚቀጥሉት ቀናት ከቱርክ በኩል በርካታ ስደተኞች ወደ አዉሮጳ ሕብረት ድንበር እንደሚጎርፍ «ፍሮንቴክክስ » የተባለዉ የአውሮጳ የድንበርና የደሴቶች ተቆጣጣሪ ድርጅት አስጠነቀቀ። «ዲ ቬልት የተሰኘዉ» የጀርመን ዕለታዊ ጋዜጣ ዛሬ እንደዘገበው ከሆነ ከቱርክ በኩል የሚፈልሰው ከፍተኛ ቁጥር ስደተኛ አውሮጳዊትዋ ሀገር ግሪክ  የሚገባ ነው። ከቱርክ በኩል ወደ ግሪክ የሚገባውን ከፍተኛ ቁጥር  ያለውን ስደተኛ ለመያዝ እጅግ ከባድ እንደሚሆን ፍሮንቴክስ የተባለው የአውሮጳ ሕብረት የድንበር ተቆጣጣሪ ድርጅት አስታውቋል። የጀርመኑ የክርስትያን ዴሞክራቶች ኅብረት ፓርቲ እጩ ሊቀመንበር ፍሬድሬሽ ሜርዝ እንደሚሉት ጀርመን ስደተኞችን መርዳት ይኖራባታል ግን ፤ 
«ፌደራል ሬፓብሊክ ጀርመን መርዳት ይኖርበታል ፤ እንደዉም እስከዛሬ ከረዳዉ የበለጠ እርዳታ ይኖርበት ይሆናል። ይሁንና ይሄን ሲያደርግ ግን ጀርመን ስደተኞቹን መቀበል እንደማይችል ለስደተኞቹ ማሳወቅ ይኖርበታል። ወደ ጀርመን መምጣቱ ምንም አይነት ዋጋ እንደሌለዉ ወደ ጀርመን ብትመጡም እንደማንቀበላችሁ ልታዉቁ ይገባል ብሎ  መግለጽ ያስፈልጋል። »
ስደተኞች በዝተዉብኛል ፤ ለስደተኞች የተገባልኝ ገንዘብ አልተከፈለኝም የምትለዉ ቱርክ ፕሬዚዳንት ራቺብ ታይብ ኤርዶዋን በበኩላቸዉ፤ ገንዘቡን መራሂተ መንግሥትዋን ጠይዪያቸዉ ነበር ባይ ናቸዉ።  
ለመራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል ባለፈዉ በጋ ወራት ይህን ያህል ገንዘብ እንደሚሰጡን ቃል ገብተዉልን ነበር። ነገር ግን በመጨረሻ ይሰጣል የተባልነዉ ገንዘብ 25 ሚሊዮን ይሮ ብቻ ነዉ። በመጨረሻ ይህን ገንዘብ የምንሰጠዉ የቀi መስቀል ነዉ ተባለ። ቢሆንም ገንዘቡ እስካሁን አልደረሰንም ደግሜ ደዉይ ስለገንዘቡ ጠየኩዋቸዉ። ገንዘቡ ሊሰጥ ዝግጁ ነዉ አሉኝ ። እናም ማለት የምፈልገዉ ገንዘቡን ልትሰጡን ከፈለጋችሁ ስጡን ነዉ። 
በጎርጎረሳውያኑ 2016 የአውሮጳ ሕብረት ከቱርክ ጋር በደረሰዉ ስምምነት መሰረት ቱርክ በሀገርዋ ያሉትን ስደተኞች እዝያው እንድትይዝ ይጠበቃል። የተመ ድርጅት ይፋ ባደረገዉ መረጃ መሰረት ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ ቅዳሜ ቱርክ ስምምነቱን  በማፍረስ ከአዉሮጳዊትዋ ሀገር ግሪክ ጋር ያላትን ድንበር አላልታ  ቢያንስ 13 ሺህ ስደተኞች በግሪክዋ ደሴት ሌስቦስ አቅራብያ ተሰብስበው ይገኛሉ። ወደ ደሴትዋ ለመግባት በጎማ ጀልባ ተሳፍረው ከነበሩ ሰዎች መካከል አንድ ሕጻን ባሕር ውስጥ ሰጥሞ ሕይወቱ ማለፉም ተነግሮአል።  ግሪክ በበኩልዋ ወደ ድንበርዋ የተጠጉትን በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ወደ ድንበርዋ ዘልቀዉ እንዳይገቡ በአስለቃሽ ጢስ እያባረረች ነው። ተጨማሪ ስደተኛ ለማስጠለል አቅም እንደሌላት የገለፀችው ቱርክ በበኩልዋ ከ 3,6 ሚሊዮን በላይ የሶርያ ስደተኞችን ማስጠጋቷን አስታውቃለች።
 

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሰ