1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ቱሪዝምና ሰላም በኢትዮጵያ፤ በቱሪዝም ሳምንት ሲወሳ

ሐሙስ፣ መስከረም 23 2017

በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ እምቅ የቱሪዝም አቅሞች ቢኖሩም በሀገሪቱ እየተስተዋለ የሚገኘው መጠነ ሰፊ ግጭት ለዘርፉ መቀጨጭ አይነተኛ ሚና እንዳለው ይነገራል፡፡ ሆኖም ዘርፉን ለማሳደግ ሊጎበኙ የሚችሉ ስፍራዎችን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል።

https://p.dw.com/p/4lNDi
Äthiopien | Oromia Tourism Week
ምስል Seyoum Getu/DW

«ግጭት ቢኖርም እጅ አጣጥፎ መቀመጥ አይገባም » የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን

በኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ እምቅ የቱሪዝም አቅሞች ቢኖሩም በሀገሪቱ እየተስተዋለ የሚገኘው መጠነ ሰፊ ግጭት ለዘርፉ መቀጨጭ አይነተኛ ሚና እንዳለው ይነገራል፡፡
ሆኖም ዘርፉን ለማሳደግ ሊጎበኙ የሚችሉ ስፍራዎችን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚያስፈልግ ተጠቁሟል። 

ዘንድሮ በዓለማቀፍ ደረጃ የተከበረው የቱሪዝም ሳምንት ዋነኛ መርህውን ሰላም ለቱሪዝም በሚል ሰላምና ጸጥታ ለዘርፉ ያለውን አበርክቶ በማጉላት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ የቱሪዝም እንቅስቃሴው የሚጎላበት ዋነኛ ወቅት በሆነው በዚህ መስከረም ወር በርካታ የቱሪስት መስዕብ ሁነቶች ይከናወናሉ፡፡

የቱሪዝም አቅምና የጸጥታው ፈተና

ብሪያን ሜይ በሰሜን ብሔራዊ ፓርኮች የመሬት ገጽታ ፕሮጀክት አስተባባሪና የቱሪዝም ባለሙያ ናቸው፡፡ ባለሙያው አስተያየታቸውን የጀመሩት ቱሪዝም ባለው ሰዎችን የማገናኘት ትልቅ አቅሙ ነው፡፡ “ቱሪዝም ሰዎችን የማገናኘት ሰፊ እድል ይፈጥራል፡፡ በዚህም መተማመንን የሚፈጥር ግንኙነትንም የመፍጠር አቅም ያለው ዘርፍ ነው፡፡ ያ ደግሞ ቱሪዝም ሰላም እንዲፈጠር ከማድረግ አኳያ ጉልህ አበርክቶ እንዳለው የሚያሳይ ነው፡፡

ግጭት ያቆረቆዘው ቱሪዝም

ይህን ብዙ ጥቅም ያለውን ቱሪዝም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያቀዘቀዘው አንድም የሰላም ሁኔታ ሲሆን በዋናነት ግን በየትኛውም ዓለም የኮቪድ ዓለማቀፍ ወረርሽን በአጠቃላም የተጓዦችን እንቅስቃሴ ከገደበ ወዲህ እስካሁን ወደ ቦታው ሊመለስ አልቻለም፡፡ በታሪካዊ፣ ባህል እና በዱር እንስሳት ሃብቷ ትልቅ አቅም ያለው እንደ ኢትዮጵያ ያለ አገር ግን ከዘርፉ ለመጠቀም የቱሪዝም መሰረተ ልማቶችን መገንባትና ማስተዋወቅ ይጠበቅበታል” ብለዋል፡፡

የቱሪዝም እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ
ብዙ ጥቅም ያለውን ቱሪዝም አሁን ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ያቀዘቀዘው አንድም የሰላም ሁኔታ ሲሆን በዋናነት ግን በየትኛውም ዓለም የኮቪድ ዓለማቀፍ ወረርሽን በአጠቃላም የተጓዦችን እንቅስቃሴ ከገደበ ወዲህ እስካሁን ወደ ቦታው ሊመለስ አልቻለምምስል Seyoum Getu/DW

የፊታችን ቅዳሜ እና እሁድ በአዲስ አበባ እና ቢሾፍቱ ከተሞች የሚከበረውና በርካቶች ይታደሙበታል ተብሎ የሚጠበቀውን የኢሬቻ በዓልን ምክንያት በማድረግ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን የቱሪዝም ሳምንትን እያከበረ ይገኛል፡፡ ባለድረሻ አካላትን አሰባስቦ በፓናል ውይይቶች እና አውደ ርዕይ እየተከበረው በሚገኘው በዚህም ሁነት ቱሪዝም እና ሰላም ያላቸው ቁርጭት በጉልህ ተወስቷል፡፡

የአገር ጎብኒዎች ቪዛ ማጠር በቱሪዝም ላይ ያሳደረው ተጽእኖ

አቶ ነጋ ወዳጆ የኦሮሚያ ቱሪዝም ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ናቸው፡፡ እንደሳቸው አስተያየት ኮሽታን ለማይወደው የቱሪዝም ዘርፍ ልማት ግጭቶች ያላቸው አሉታዊ ውጤት በግልጽ የሚታወቅ ብሆንም እጅ ግን አጣጥፎ መቀመጥ አያስፈልግም፡፡ “በርግጥ ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ኦሮሚያ ውስጥ ግጭት ያለባቸው ቦታዎች አሉ፡፡ ግጭት ከሚኖርባቸው የአገሪቱ አከባቢዎች ግን ሰላም ያለባቸውም በርካታ ነውና እነዚያን በማጉላት ማስተዋወቅ ያስፈልጋል ብለን ቱሪዝም ሰላምን መጣል በሚል እየሰራን እንገኛለን” ብለዋል፡፡ የሰዎች እንቅስቃሴ ሰላምን ከማምጣት አኳያ ያለውን ሚና በማጉላትም አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

ያልታየው የቱሪዝም መስህብ፤ የጅማው ሰቃ ፏፏቴ

አቶ ነጋ በኢትዮጵያም ሆነ በኦሮሚያ ክልል እየተስተዋለ ለው ግጭት አለመረጋጋት በቱሪዝም ዘርፉ ላይ ያሳደረውን ጥላ ስያስረዱም፤ “በየትኛውም ኣለም እንደሚሆን ለቱሪስት አደጋ የሚሆኑ ክስተቶች ቢያጋጥሙም ጎልቶ የሚነገረው እነዚያ ግጭቶች የመሆኑ ጉዳይ ዘርፉን ጎድቶታል” ብለዋል፡፡ አቶ ነጋ በኢትዮጵያ በርካታ ልጎበኙ የሚችሉ ሰላማዊ አከባቢዎች መኖራቸውንም አንስተው በተለይም የአገር ውስጥ ቱሪዝም ላይ በርካታ ስራዎች መሰራታቸውን ገልጸዋል፡፡ ኃላፊው ከግጭት ጋር ተያይዞ የሚነሱ አሉታዊ ጉዳዮች ቱሪዝም ኢንደስትሪውን መጉዳቱን ግን አያስተባብሉም፡፡

በኢትዮጵያ በተለይም በተሰሜን የአገሪቱ አከባቢዎች፣ በምእራብ እና በተለያዩ ግጭት በሚነሳባቸው አከባቢዎች በቱሪዝም ጭምር የሚተዳደሩ አከባቢዎች ባለፉት አምስት ኣመታት ገደማ ፈተና ውስጥ መግባታቸውም እንዲሁ ይነሳል፡፡

ሥዩም ጌቱ

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ