ተፈሪ ፈቃደ እና የበጎ ፈቃድ ሥራው | ባህል | DW | 19.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ተፈሪ ፈቃደ እና የበጎ ፈቃድ ሥራው

አርቲስቶችን ለመርዳት የተመሰረተው ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርቲስቶች ማዕከል» ሊቀመንበር ተፈሪ ማህበሩ እንዲቋቋም ምክንያት ከሆኑት ሰዎች እንዲሁም ከመሥራቾቹ አንዱ ነው ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 12:54

ተፈሪ ፈቃደ

 

ተፈሪ ፈቃደ «ትሪለር» በተሰኘው የማይክል ጃክሰን ዘፈን በመደነስ ሙዚቃው በወጣበት በ1970ዎቹ  ኢትዮጵያ ውስጥ እውቅና ያተረፈ ዳንሰኛ ነበር ። በዳንሴ ከማይክል ጃክሰን ሳልበልጥም አልቀር ይላል ።  ጀርመን ፍራንክፈርት አቅራቢያ በምትገኘው ዳርምስታት በተባለችው ከተማ ውስጥ የሚኖረው ተፈሪ ይበልጡን የሚታወቀውም በኢትዮጵያ በጤና ችግር በአቅም መድከምም ሆነ በሌሎች ችግሮች ውስጥ ለሚገኙ አርቲስቶች መርጃ ለተቋቋመው ማህበር በሚያደርገው የበጎ ፈቃድ ሥራ ነው ። ዓላማውን ከሚደግፉ ሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር እዚህ ጀርመን በየዓመቱ ለማህበሩ መርጃ የሚውል  የሙዚቃ ፌስቲቫል ያዘጋጃል ። አርቲስቶችን ለመርዳት የተመሰረተው ፣የኢትዮጵያ ብሔራዊ አርቲስቶች ማዕከል» ሊቀመንበር ተፈሪ ማህበሩ እንዲቋቋም ምክንያት ከሆኑት ሰዎች እንዲሁም ከመሥራቾቹ አንዱ ነው ።ይኽው ማህበር በጥቂት ዓመታት ውስጥ የጥረቱን ፍሬ ለማየት በቅቷል ።

ኂሩት መለሰ

ልደት አበበ

Audios and videos on the topic