ተጫዋቾቹ በርሊን ገቡ | ስፖርት | DW | 15.07.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ስፖርት

ተጫዋቾቹ በርሊን ገቡ

የቡድኑ አባላት በግልፅ መኪና ተሳፍረዉ ከበርሊን አዉሮፕላን ማረፊያ ዋናዉ ድግሥ-ሥፍራ ብራንደርቡርገር ቶር እስኪደርሱ ድረሥም በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በመንገዶች ግራና ቀኝ በመሆን የጀግና አቀባበል አድርጎላቸዋል

የዘንድሮዉን የዓለም እግር ኳስ ዋንጫ የወሰደዉ የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አባላት ዛሬ ቀጥር ላይ ጀርመን ርዕሠ-ከተማ በርሊን ገቡ።ለብሔራዊ ቡድኑ ክብር ከታሪካዊዉ የብራንደርቡርገር ቶር አካባቢ በተዘጋጀዉ የአቀባበል ሥነ-ሥርዓት ከአራት መቶ ሺሕ የሚበልጥ እግር ኳስ አፍቃሪ ተገኝቷል።የቡድኑ አባላት በግልፅ መኪና ተሳፍረዉ ከበርሊን አዉሮፕላን ማረፊያ ዋናዉ ድግሥ

ሥፍራ ብራንደርቡርገር ቶር እስኪደርሱ ድረሥም በብዙ ሺሕ የሚቆጠር ሕዝብ በመንገዶች ግራና ቀኝ በመሆን የጀግና አቀባበል አድርጎላቸዋል።

የብራንደን ቡርግ በር በተሠራው 230 ሜትር ርዝማኔ ባለው መድረክ፤ በዘንድሮ የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አስተናጋጅ ሀገር፤ ብራዚል ብሔራዊ ቋንቋ ፖርቱጋልኛ «ኦብሪጋዶ! ደጋፊዎቻችን፤ 4ኛው ኮከብ የኛ ሆኗል » የሚል መፈክር በጉልህ ተጽፎ ይነበብ ነበር። «ኦብሪጋዶ» በፖርቱጋልኛ «እናመሰግናለን » ማለት ነው።

የጀርመን ብሔራዊ ቡድን አሠልጣኝ ዮአኺም ሎዖቭ፣ ኳስ አፍቃሪዎችን ሁሉ በማመሥገን፣ ያለእናንተ ድጋፍ የትም አንደርስም ነበረ ብሏል።

«ብዙ ጊዜ ቢያስጠብቅም በመጨረሻ የዓለም ሻምፒዮን ለመሆን በቅተናል።»

የብሔራዊውን ቡድኑን ተጫዋቾች ለመቀበል፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎችና ከተሞች ወደ በርሊን ከተጓዙት መካከል «የደጋፊዎች አንድ ማይል ጎዳና» በተሰኘው ቦታ የተገኘች አንዲት አድናቂ እንደተናገረችው ለተጫዋጮቹ አቀባበል በሚደረግበት ቦታ የደረሰችው ሌሊት ነው።

«3 ሆነን እኩለ ሌሊት ላይ ወደ በርሊን ጉዞ ጀመርን፤ ከሥራ ለመቅረት የአጭር ጊዜ ፈቃድ አግኝተን ነበር። በጨለማ ተጉዘን ከሌሊቱ 9 ሰዓት ተኩል በርሊን ገባን። የልባችን ትርታ ይፈጥን ጀመር። እጅግ ደስ ብሎናል። እርግጥ በአንቅልፍ እጦትና በድካም ድቅቅ ብለናል፤ ልክ እንደ እግር ኳስ ተጫዋቾቹ ወጣት ጀግኖች! ይሁን እንጂ፤ ለመቀበል መዘጋጀታችን ይህ ነው የማይባል ደስታ ነው የፈጠረልን። የቴሌቭዥኑን ተንቀሳቃሽ ምስል፤ ትልቅ ግድግዳ ላይ ማየቱ፣ እፁብ ! እፁብ ድንቅ ነው»

የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤልን በሥልክ አነጋግረነዋል።

ይልማ ሐይለ ሚካኤል

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic