ተባብሶ የቀጠለዉ የሱዳን ፀረ-መንግሥት ተቃዉሞ | አፍሪቃ | DW | 09.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ተባብሶ የቀጠለዉ የሱዳን ፀረ-መንግሥት ተቃዉሞ

በጎርጎሮሳዊዉ ታኅሣስ 19፣ 2018 በሸቀጣ ሸቀጦች ዋጋ ንረት ሳቢያ በሱዳን መዲና ካርቱም የተቀሰቀሰዉ ተቃዉሞ ቀስበቀስ ሌሎች የሀገሪቱን ከተሞች እያዳረሰ ነዉ። ተቃዉሞዉ ከኢኮኖሚ ጥያቄ አልፎ የፓለቲካ መልክ መያዝ ጀምሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:09
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:09 ደቂቃ

ፀረ-አልበሽር ተቃዉሞዉን ሙህራንም ተቀላቅለዉታ።

 የተቃዉሞ አመፁ ብዙዎችን  ለአካል ጉዳትና ለሞት እየዳረገ በመሆኑም የሀገሪቱ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና ሙህራን እንዲሁም በአለም አቀፍ ተቋማት የአልበሽርን መንግስት እየተቹ ነዉ።ትችት የበረታባቸዉ ፕሬዳንቱ በዛሬዉ ዕለት ስልጣናቸዉን ለማስረከብ መዘጋጀታቸዉን ነገር ግን ይህ በምርጫ ብቻ እውን እንደሚሆን ለደጋፊዎቻቸዉ ገልፀዋል።
ሶስተኛ ሳምንቱን የያዘዉ የሱዳን ፀረ-መንግስት ተቃዉሞ በዛሬዉ ዕለትም በመዲናዋ ካርቱምና በኦምዱራማን ከተማ ቀጥሎ ነዉ የዋለዉ፣ የዜና ምንጮች እንደዘገቡትም፣ ፖሊስ በኦምዱርማን በተቃዋሚዎች ላይ አስለቃሽ ጭስ ተኩሷልል። በነዳጅና በዳቦ ዋጋ ማሻቀብ ሰበብ የተቀሰቀሰዉ ህዝባዊ ተቃዉሞ  ቀስበቀስ ሌሎች ከተሞችን እያዳረሰ፤ የሀገሪቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎችና  የምህራንን ድጋፍ እያገኘ መምጣቱ እየተነገረ ነዉ። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ችግሩን ለመፍታት መርማሪ ኮሚሽን አቋቁሚያለሁ ቢሉም የሰማቸዉ የለም። ይልቁንም  አመፁ ብዙዎችን  ለአካል ጉዳትና ለሞት እየዳረገ ቀጥሏል። 


ይህንን ተከትሎም ያለፈዉ ሳምንት መጀመሪያ ላይም 22 የተቃዋሚ ፓለቲካ ፓርቲዎችና ማህበራት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽር ስልጣናቸዉን በመልቀቅ የሽግግር መንግስት እንዲቋቋም ጠይቀዋል።ራሳቸዉን የለዉጥ ብሄራዊ ህብረት ብለዉ የሰየሙት እነዚህ ፓርቲዎች ፕሪዚዳንቱ ለሀገሪቱ ሎአላዊ ምክር ቤት ስልጣናቸዉን እንዲያስረክቡ ፤ያ ካልሆነ ግን ሀገሪቱ ወደ ቀዉስ ልታመራ ትችላለች ሲሉ ነበር ያስጠነቀቁት።ፕሬዚዳንቱ ግን ተቃዉሞዉን የዉጭ አካላት ከጀርባዬ የሸረቡብኝ ሴራ ነዉ ሲሉ ነበር ያጣጣሉት።  በተቃዉሞ የተሳተፉ ወጣቶችንም «ቅጥረኞች » በሚል ወንጀል ለዕስር ዳርገዋቸዋል።ከትናንት በስቲያም በርካታ የካርቱም ዩንቨርሲቲ መምህራን አመጹን ደግፋችኋል በሚል መታሰራቸዉ ተሰምቷል። የሱዳን የሀገር ዉስጥ ሚንስትር ቢላል ኦስማን ያለፈዉ ሰኞ እንደገለፁትም ከተቃዉሞዉ ጋር በተያያዘም  ከ800 በላይ ሰዎች በቁጥጥር ስር ዉለዋል።ተቃዉሞዉን ለመግታት የመንግስት የፀጥታ ሀይሎች  በወሰዱት ርምጃም የሞትና የአካል ጉዳት ተከስቷል።ያም ሆኖ ግን  የሀገር ዉስጥ ሚንስትሩ ቢላል ኦስማን ግጭቱ ሳይባባስ በቁጥጥር ስር ዉሏል ሲሉ ነበር የተደመጡት።


"የፖሊስ እና የፀጥታ ሀይሎች ትኩረት የህገወጦችን ጥቃት ማስቆምና እነዚህን  መጥፎ አጋጣሚዎች በመገደብ የከተሞችን ሰላም ወደ ነበረበት መመለስ ላይ ያተኮሩ ናቸው።ትናንሽ ሁነቶች ትልቅ ደረጃ ከመድረሳቸዉና ለሌላ ዓላማ ከመዋላቸዉ  በፊት በቁጥጥር ስር ዉለዋል። »ነዉ ያሉት የሱዳን የሀገር ዉስጥ ሚንስትር አህመድ ቢላል ኦስማን።
 በሱዳን  ፀረ- መንግስት ተቃዉሞ ምንም እንኳ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች የሟቾችን ቀጥር 37 ቢያርሱትም 19 ሰዎች መገደላቸዉን መንግስት አምኗል።እንዲያም ሆኖ ፕሬዝዳንት አልበሽር ባለፈዉ ሳምንት ለደጋፊዎቻቸዉ ባሰሙት ንግግር ችግራችን ጊዚያዊ ነዉ ነበር ያሉት ።
« በምታዉቁት ዉስጣዊና ዉጫዊ ምክንያቶች ሀገራችን  በርካታ ህብረተሰባችንን ጉዳት ላይ በጣለ አስቸጋሪ የኢኮኖሚ ሁኔታ ዉስጥ ትገኛለች። ነገር ግን ይህንን ጊዜያዊ ችግር ለመወጣት መቃረባችንን እንተማመናለን።»


እሳቸዉ ይህንን ይበሉ እንጅ የፖለቲካ ተንታኙ አቶ አበበ አይነቴ እንደሚሉት ግን  ችግሩ ዉስብስብና በቀላሉ ለመፍታት የሚያዳግት ነዉ።
ምክንያቱም አሉ አቶ አበበ «የተቃዉሞ አመፁ ለበርካታ አመታት በተጠራቀሙ ችግሮች የመጣ ነዉ»።
ይህንን በመገንዘብ ይመስላል ከስልጣን ይልቀቁ ግፊት የበረታባቸዉ ፕሬዳንቱ በዛሬዉ ዕለት ስልጣናቸዉን ለማስረከብ መዘጋጀታቸዉን ነገር ግን ምርጫ እንዲካሄድ ለደጋፊዎቻቸዉ ገልፀዋል።
የቀድሞዉን ፕሬዚዳንት አህመድ አልሚርጋህን በመፈንቅለ መንግስት አስወግደዉ ከ ሃያ ዘጠኝ ዓመት በፊት በጎርጎሮሳዉያኑ 1989 መንበረ ስልጣንኑን የተቆጣጠሩት የ75 ዓመቱ ፕሬዚዳን ኦማር አልበሽር በአሁኑ ወቅት በመንግስታቸዉ ላይ የተቀሰቀሰዉን የተቃዉሞ አመፅ ከተሻገሩ በመጭዉ ሰኔ የ30ኛ ዓመት በዓለ ሲመታቸዉን ሊያከብሩ ይችላሉ።የመጣባቸዉ የተቃዉሞ ወጀብ ግን እንደ ፖለቲካ ተንታኞቹ ቀላል አይመስልም። 

 

ፀሐይ ጫኔ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic