ተቃውሞ የቀጠለባት ሊቢያ | ኢትዮጵያ | DW | 26.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ተቃውሞ የቀጠለባት ሊቢያ

በሊቢያ መሪ ኮሎኔል ሙአመር ኧል ጋዳፊ አንጻር ካለፈው ሳምንት ወዲህ የተጀመረው የህዝብ ተቃውሞ ዛሬም በብዙ የሀገሪቱ ከፊል ተስፋፍቶ ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

default

ተቃዋሚዎች በራስ ላኑፍ ከተማ በስተምስራቅ የሚገኙትን የነዳጅ ዘይት ንጣፎች በጠቅላላ መቆጣጠራቸው ተሰምቶዋል። በዓለም በነዳጅ ዘይት አምራችነትዋ የአስራ ሰባተኛነቱን፡ በአፍሪቃ ደግሞ የሶስተኛነቱን ቦታ ለያዘችውን ለሊቢያ መሪ ኮሎኔል ሙአመር ኧል ጋዳፊን እስከ ቅርብ ቀናት በፊት ድረስ ታማኝ ሆነው የቆዩት ብዙዎቹ የሀገሪቱ ጎሳዎች አሁን ይህንኑ ድጋፋቸውን አቋርጠው ተቃውሞውን ተቀላቅለዋል።

ዶይቸ ቬለ
አርያም ተክሌ