ተቃውሞ ለንደን በሚገኘው የሊቢያ ኤምባሲ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.12.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ተቃውሞ ለንደን በሚገኘው የሊቢያ ኤምባሲ

በሊቢያ ያለውን የአፍሪቃውያን ባርነት በመቃወም ዛቴ የብሪታንያ መዲና ለንደን ከተማ በሚገኘው የሊቢያ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። የተቃውሞ ሰልፉ የተጠራው «ብሔራዊ ጸረ-ባርነት» በተባለው ግብረ-ኃይል ነው። በተቃውሞ ሰልፉ አያሌ ኢትዮጵያውያንም ተሳታፊ ነበሩ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:29

በሊቢያ ያለውን ባርነት በመቃወም የለንደን ሰልፍ

በሊቢያ የሚገኘውን የአፍሪቃውያን ባርነት በመቃወም ዛሬ የብሪታንያ መዲና ለንደን ከተማ በሚገኘው የሊቢያ ኤምባሲ ደጃፍ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሂዷል። የተቃውሞ ሰልፉ የተጠራው «ብሔራዊ ጸረ-ባርነት» በተባለው ግብረ-ኃይል ነው። ተቃውሞው በተለይ በአፍሪቃ ምድር ባርነት ሲከወን የአፍሪቃ ኅብረት ቸልተንነት በመንቀፍ ያተኮረ ነበር። በብሪታንያ እና በፈረንሳይ መንግሥት ላይ ሰልፈኞች ቁጣቸውን ገልጠዋል። ምስቅልቅሏ በወጣው ሊቢያ ውስጥ አፍሪቃውያን በሊቢያ ዜጎች ለባርነት እየተሸጡ ነው የሚለው ዜና በቪዲዮ ታጅቦ በሲኤን ኤን ማሰራጪያ በኩል ይፋ ከወጣ በኋላ የተቀሰቀሰው ቁጣ ከየአቅጣጫው አልበረደም። በተቃውሞው ላይ በርካታ ኢትዮጵያውያንም ተሳታፊ ነበሩ። ድልነሳው ጌታነህ ሰልፉ በተካሄደበት ሥፍራ ተገኝቶ ያጠናቀረውን ዘገባ ከለንደን ልኮልናል።

ድልነሳው ጌታነህ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

Audios and videos on the topic