ተቃውሞና የወጣቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ | ባህል | DW | 12.08.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ተቃውሞና የወጣቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ

በዛሬው የወጣቶች መሰናዶ እሸቴ በቀለ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ተቃውሞዎች ላይ አተኩሯል። በመሰናዶው ጦማሪው በፍቃዱ ኃይሉ እና የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ወጣት ነጂባ አክመልን አነጋግሯል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:06

ተቃውሞና የወጣቶች ተሳትፎ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀሰቀሰው ተቃውሞ በማህበራዊ-ድረ ገጾች የሚደረጉ ውይይቶችን ተቆጣጥሯል። በአብዛኛው ወጣቶች የሚበዙበት የማህበራዊ ድረ-ገጾች ለወቅታዊው የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ ከሌሎች የመገናኛ ብዙኋን ተመራጭ የሆኑ ይመስላል። በውይይቶቹ እና ክርክሮቹ የጸጥታ ኃይሎች በተቃዋሚዎች ላይ የወሰዱትን እርምጃ የሚያወግዙ አስተያየቶች ይበዛሉ። የዛኑ ያክል ተቃውሞዎቹን የሚያወግዙም አልጠፉም።

የአዲስ አበባ ኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ ሊቀመንበር ወጣት ነጂባ አክመል በተለያዩ አካባቢዎች በተቀሰቀሱ ተቃውሞቆች የተሳተፉ ወጣቶች ጥቂት ናቸው የሚል እምነት አላቸው።

ፀሃፊው፤የሰብዓዊ መብት አራማጁ እና ጦማሪው በፍቃዱ ኃይሉ አሁን የኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታን ከሚከታተሉ አንዱ ነው።

በፍቃዱ በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በሚታየው የአደባባይ ተቃውሞ የማህበራዊ ድረ-ገጾች ከፍ ያለ ሚና መጫወታቸውን ይናገራል።

እሸቴ በቀለ

ሒሩት መለሰ

Audios and videos on the topic