ተቃዉሞና የህዝብ አመፅ በየመን | ዓለም | DW | 09.02.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ተቃዉሞና የህዝብ አመፅ በየመን

በቱኒዚያና በግብፅ የተቀጣጠለዉን ህዝባዊ አመፅ ተከትሎ በየመንም ተቃዋሚዉ ወገን ወደ20ሺ የተገመተ ህዝብ አደባባይ ወጥቶ ድምፁን እንዲያሰማ ማድረግ ተሳክቶለታል።

default

ለተቃዉሞ የወጣዉ ህዝብ በሰንዓ

ትናንት ፈረንሳይ የተገኙት የአገሪቱ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቡበከር አል ቂርቢ ግን የየመኑ የህዝብ ተቃዉሞ ከሌሎቹ አገራት እንደሚለይ ተናግረዋል። እንደእሳቸዉ ከሆነም የየመን መንግስት ከቱኒዚያና ግብፅ መንግስታት በተለየ በአገሪቱ ከሚገኙ የተቃዉሞ ፖለቲካ ኃይሎች ጋ ለመነጋገር ዝግጁነት አጥሮት አያዉቅም። በዚህም ምክንያት ከቱኒዚያ ቤን አሊን አባሮ ወደግብፁ ሆስኒ ሙባረክ ያነጣጠረዉ ዓይነት ህዝባዊ አመፅ ፕሬዝደንት አሊ አብዱላሂ ሳልህ ይገጥማቸዋል ብለዉ አይገምቱም። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ የፖለቲካ ተንታኞች ግን በዚህ ሁኔታ ፕሬዝደንት አሊ ስልጣን፤ ገንዘብና ደህንነት ያጣሉ እያሉ ነዉ።

አነ አልመሊንግና፤ ዮሃንስ ኩርግ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

ተዛማጅ ዘገባዎች