ተቃዉሞና ኃይል የቀላቀለ ግጭት በፓሪስ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 16.03.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ተቃዉሞና ኃይል የቀላቀለ ግጭት በፓሪስ

በፈረንሳይ «ቢጫ ሰደርያ» በመባል የሚታወቀዉ የተቃዉሞ ንቅናቄ ዛሬ ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ላይ ዳግም ማገርሸቱ ተነገረ። በተቃዉሞዉ ከፍተኛ ኃይል የቀላቀለ ረብሻና ቃጠሎ ታይቶአል። የተቃዉሞ ሰልፉ ሰላማዊ ሆኖ ቢጀመርም አንዳንድ ረብሻ ቀስቃሾች አጋጣሚዉን በመጠቀም ሰልፉን ወደ ረብሻ ሲቀይሩት ታይቶአል።

 

በፈረንሳይ «ቢጫ ሰደርያ» በመባል የሚታወቀዉ የተቃዉሞ ንቅናቄ ዛሬ ፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ላይ ዳግም ማገርሸቱ ተነገረ። በተቃዉሞዉ ከፍተኛ ኃይል የቀላቀለ ረብሻና ቃጠሎ ታይቶአል። ግጭቱ የተፈጠረዉ በተቃዋሚ ሰልፈኞች እና ፀጥታን በሚያስከብሩ ፖሊሶች መካከል መሆኑም ተመልክቶአል። በተቃዉሞ ሰልፍ ላይ አንዳንድ ረብሻ ቀስቃሾች አጋጣሚዉን በመጠቀም ሱቆችን እና የዉድ ቁሳቁስ መሸጫ መደብሮችን ሲዘርፉና  መሬት ላይ የተነጠፈ «ኮብል ስቶን» ማለትም ድንጋዮችን እየፈነቀሉ ፖሊስ ላይ ሲወረዉሩ ታይቶአል።

ፖሊስ በበኩሉ ግጭቱን ለማስቆም ዉኃ ሲረጭና አስለቃሽ ጢስ ሲተኩስ ተስተዉሎአል። እስከ ዛሬ ቀትር ድረስ ፖሊስ በአስራዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተያይዞ ተዘግቦአል። የፈረንሳይ የሃገር አስተዳደር ሚኒስትር ክርስቶፍ ካስትነር እንደገለፁት የተደራጁና የተካኑ ዘራፊዎች በሰላማዊ ሰልፈኞቹ መካከል ተቀላቅለዋል ማለታቸዉ ተነግሮአል። ከወራቶች በፊት የፈረንሳዩን ፕሬዚዳንት የኤማኑኤል ማክሮን የፖለቲካ አቋም በመቃወምና በሃገሪቱ የነዳጅና የግብር ቅነሳን በመጠየቅ « ቢጫ ሰደርያ» በሚል በፈረንሳይ ዙርያ የተቃዉሞ ንቅናቄ መቀስቀሱ የሚታወስ ነዉ። ባለፉት ወራቶች በፈረንሳይ በተለይ በፓሪስ ከተማ በታየዉ የ«ቢጫ ሰደርያ » የተቃዉሞ ሰልፎች በርካታ መኪኖች መቃጠላቸዉ፣ የሱቅ መስኮቶች መሰባበራቸዉ ይታወቃል። 

 

አዜብ ታደሰ

ልደት አበበ

ተዛማጅ ዘገባዎች