ተሸናፊው ያሕያ ጃሜሕ ስልጣን ለማስረከብ ተስማሙ | አፍሪቃ | DW | 21.01.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ተሸናፊው ያሕያ ጃሜሕ ስልጣን ለማስረከብ ተስማሙ

በጋምቢያ በተካሄደው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የተሸነፉትና ውጤቱን ለመቀበል አሻፈረኝ ሲሉ የሰነበቱት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ያሕያ ጃሜሕ ዛሬ ከስልጣን እንደሚወርዱ ተናገሩ፡፡

ትናንት ማምሻውን ፕሬዘዳንቱ ይህን በመንግስታዊው ቴሌቪዥን ጣቢያ የተናገሩት ከጊኒው ፕሬዝዳንት አልፋ ኮንዴ እና ከሞሪታኒያው አቻቸው ሞሐመድ አብዱል አዚዝ ጋር ከተነጋገሩ በኋላ ነው፡፡ ሁለቱ ፕሬዝዳንቶች ወደ ጋምቢያ ያቀኑት የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት ለጉዳዩ ዕልባት ለመስጠት ተደጋጋሚ ሙከራ አድርገው ከከሸፈባቸው በኋላ ነው፡፡ የጃሜሕን እምቢተኝነት በኃይል ለመቀልበስ የተንቀሳቀሱት ሁለቱ የምዕራብ አፍሪቃ ሀገራት- ናይጄሪያ እና ሴኔጋል - 7000 የሚጠጉ ወታደሮቻቸውን ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ወደ ጋምቢያ ልከዋል፡፡

Gambia Machtwechsel - Präsident Adama Barrow in Dakar, Senegal

የጋምቢያው አዲስ ፕሬዚዳንት አዳማ ባሮው

በታንኮች እና ተዋጊ አውሮፕላኖች የተደገፈው የሁለቱ ሀገራት ጦር ወደ ጋምቢያ ሲገባ ከጃሜህ ሰራዊት ምንም አይነት መከላከል እንዳልገጠመው ተዘግቧል፡፡ የወታደሮቹ አካሄድ ምርጫ ያሳጣቸው የሚመስሉት ጃሜህ ከስልጣናቸው ለመልቀቅ የወሰኑት ለ“ሀገር ጥቅም” ሲሉ እንደሆነ አሳውቀዋል፡፡ ሀገሪቱ በገባችበት የፖለቲካ አጣብቂኝ ምንም ዓይነት ደም መፋሰስ አለመከሰቱንም አወድሰዋል፡፡ ወደ ሌላ ሀገር ይሰደዱ አሊያም በሀገር ቤት ይቆዩ እንደሁ በንግግራቸው ፍንጭ አልሰጡም፡፡ የጃሜህን ውሳኔ ተከትሎ ምርጫው ያሸነፉት እና ሐሙስ ዕለት ሴኔጋል በሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ ቃለ-መሃላ የፈጸሙት አዳማ ባሮው ወደ ባንጁል እንደሚመለሱ ተዘግቧል፡፡ 

እሸቴ በቀለ

ልደት አበበ