ተስፋና ሥጋት የደቀነዉ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 22.02.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ተስፋና ሥጋት የደቀነዉ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ

በኢትዮጵያ ከዓንድ ዓመት ግድም ወዲህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረዉ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ተሃድሶ እና እየታየ ያለዉ ለዉጥ አሁንም የዓለምን ኅብረተሰብ ትኩረት መሳቡን እንደቀጠለ ነዉ። በኢትዮጵያ ከሚታዩት ለዉጦችና ተስፋዎች ጀርባ ምን እየተካሄደ ይሆን? ሃገሪቱስ የትኛዉን አቅጣጫ ይዛ እየተጓዘች ይሆን?

በኢትዮጵያ ከዓንድ ዓመት ግድም ወዲህ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የተጀመረዉ የፖለቲካና የኤኮኖሚ ተሃድሶ እና እየታየ ያለዉ ለዉጥ አሁንም የዓለምን ኅብረተሰብ ትኩረት መሳቡን እንደቀጠለ ነዉ። በኢትዮጵያ ከሚታዩት ለዉጦችና ተስፋዎች ጀርባ ምን እየተካሄደ ይሆን? ሃገሪቱስ የትኛዉን አቅጣጫ ይዛ እየተጓዘች ይሆን? የሚሉትና አሁን ያለዉን የኢትዮጵያ መንግሥት ወቅታዊ የፖለቲካ እና ኢኮኖሚ ክዋኔዎችን በተመለከተ በፈረንሳይ ዓለም አቀፍ  ግንኙነት ተቋም አዘጋጅነት ትናንት ፓሪስ ላይ ጉባዔ ተካሂድዋል። በዚሁ ጉባዔ ላይ የኦሮሞ ፊደራልሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ፕሬዚደንት ፕሮፊሰር መረራ ጉዲናን ጨምሮ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በቅርበት የሚሰሩ ፈረንሳዉያን ምሑራን ጥናታዊ ጽሑፎቻቸዉን አቅርበዋል። ጉባዔዉ ለዉጥና ተስፋን ያነገበዉ የኢትዮጵያ ወቅታዊ ፖለቲካ አሁንም ስጋቶች የተደቀኑበት መሆኑን አዉስቶአል። ቦታዉ ላይ የነበረችዉ የፓሪስዋ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ ተጨማሪ ዘገባ ልካልናለች።   

 

ሃይማኖት ጥሩነህ   

አዜብ ታደሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች