ተሪዛ ሜይ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 13.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ተሪዛ ሜይ አዲሷ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር

ባለፉት ስድስት ዓመታት በብሪታንያ ሃገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ተሪዛ ሜይ ሕዝቡ ሀገሩ ከአዉሮጳ ኅብረት እንድትወጣ ከወሰነ በኋላ ስልጣናቸዉን የለቀቁትን ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካምረንን ዛሬ በይፋ ተኩ። ካምረን ዛሬ ለፓርላማ አባላት ባሰሙት የመሰናበቻ ንግግር ተተኪዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሪዛ ሜይ ጎበዝ ተደራዳሪ መሆናቸውን ገልፀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:03

ብሪታንያ

ተሰናባቹ የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዴቪድ ካሜሩን ተተኪያቸው ቴሬሳ ሜይ ከአውሮጳ ህብረት ጋር እየተደራደሩም ግንኙነታቸውን እንዲያጠብቁ አሳስበዋል። ካሜሩን ዛሬ ለፓርላማ አባላት ባሰሙት የመሰናበቻ ንግግር ተተኪዋ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬሳ ሜይ ጎበዝ ተደራዳሪ መሆናቸውን ገልፀው ለንግድ ለትብብር እና ለፀጥታ ጥቅሞች ሲሉ በተቻለ መጠን ለአውሮጳ ህብረት ቅርብ ለመሆን እንዲሞክሩ መክረዋል። ከፍላጎት ውጭ የብሪታንያ ህዝብ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት ባሳለፈው ውሳኔ ምክንያት ከሥልጣን የወረዱትት ካሜሩን ዛሬ የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤያቸውን በበኪንግሃም ቤተ መንግሥት ለንግሥት ኤልሳቤጥ አስረክበዋል ። ከዚህ በኋላም ዘውዳዊው ስርዓት ሜይ መንግሥት እንዲመሰርቱ ሃላፊነቱን ሰጥቷቿዋል ። ባለፉት ስድስት ዓመታት የ59 ዓመትዋ ሜይ ከወግ አጥባቂ ፓርቲ ብሪታንያን በመምራት ከማርግሬት ታችተር ቀጥሎ ሁለተኛዋ ሴት ናቸው። የብሪታንያ ከአውሮጳ ህብረት መልቀቅ ደጋፊ ያልነበሩት ሜይ ብሪታንያ ከአውሮፓ ህብረት ለመውጣት በምታካሂደው ድርድር ብዙ ተግዳሮች እንደሚጠብቋቸው ይገመታል። የአውሮጳ ህብረት ባለሥልጣናት ሜይ ሂደቱን ያፋጥናሉ ብለው ተስፋ ያደርጋሉ ። ይሁንና ሜይ ወደ ይፋው ብሬኤክዚት ለመግባት እንደማይጣደፉ ነው የጠቆሙት። የፈረንሳይ ፕሬዝዳንት ፍራንሷኦሎንድ ፣ የጀርመን መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና የኢጣልያው ጠቅላይ ሚኒስትር ማቴዮ ሬንዚ በብሪታንያ ህዝበ ውሳኔ ውጤት ላይ በመጪው ጉባኤ እንደሚያካሂዱ አስታውቀዋል። አዲሷ ጠቅላይ ሚኒስትር ሜይ አዲስ የንግድ እና የጉዞ ውሎችን የማስከበር ሃላፊነት የሚሰጠው የብሬኤክዚት ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች የካቢኔ አባላትን ዛሬ ማምሻውን ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሜይ በጠቅላይ ሚንስትርነት ስልጣናቸው በመጀመሪያ ደረጃ የሚያከናውኑትስራ ምን ሊሆን ይችላል?


ድልነሳው ጌታነህ
አርያም ተክሌ
አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic