ተረት ተረት፤ የኢትዮጵያ መልካም ገፅታ | ባህል | DW | 06.03.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ባህል

ተረት ተረት፤ የኢትዮጵያ መልካም ገፅታ

አብዛኛውን ጊዜ የውጭ ሀገር ዜጎች ስለ ኢትዮጲያ ሲናገሩ ፤ሀገሪቷን በበጎ ከሆነ ፤የጥንት ሰዎች ቅሪት መገኛ፣ የቆንጆዎች ሀገር፣ የመሳሰሉት ሲሉ፤ ሌሎች ደግሞ አሁን ድረስ የ1977ቱ አይነት ድርቅ እና ርሀብ ሀገር አድርገው ይቆጥሯታል ። እናንተስ ፤ ኢትዮጵያ በውጭ ዜጎች ዘንድ ምን አይነት ገፅታ አላት ትላላችሁ?

ሀና ሰለሞን በምትኖርበት ዮናይትድ ስቴትስ፤ ሰዎች ስለ ኢትዮጵያ ጥሩ ግንዛቤ የላቸውም በማለት ይህንን ግንዛቤ እና የኢትዮጵያ ገፅታ ለመቀየር ቆርጠው ከተነሱት ወጣቶች አንዷ ናት። ከ 6 ዓመታት በፊት ከቤተሰቦቿ ጋር ወደ ዮናይትድ ስቴትስ ለመኖር ወደ ቴክሳስ የሄደችው ሀና፤ ዛሬ የ 21 ዓመት ወጣት ናት። ተረት ተረት የተባለ፤ የመገናኛ ብዙኃንን ተጠቅመው ዕውን ለማድረግ አንድ ፕሮጀክት ነድፈዋል።

ሁሉም ወጣቶች አንድ ላይ በአካል ተገናኝተው አያውቁም። አቤኔዘር ፣ማይክል እና ዮኃንስ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ሲሆኑ ፤ ሀና፣ ናሆም እና ሚኪዓለም የተባሉት ደግሞ ዮናይትድ ስቴትስ ውስጥ ናቸው። የሚገናኙት፤ ዘመን ባፈራቸው ኢሜል፤ ፌስቡክ እና ኢንስታግራም በተባሉት የመገናኛ ዘዴዎች ነው። የሃናን ህልም የሚጋራው ዮኃንስ በላይ ትምህርትቱን በይበልጥ የተከታተለው በዩናይትድ ስቴትስ ነው። ስለ አፍሪቃ በተለይም ስለኢትዮጵያ አልተማርንም ማለት ይቻላል ይላል። ሃናም አሁን በምትኖርበት ዩናይትድ ስቴትስ፤ ከትምህርት ቤት ባልደረቦቿ ጋር ስለ ሀገሯ ስታወራ፤ ስለ ኢትዮጵያ ያላቸውን እውቀት እጅግ የተወሰነ ነው ትላለች።

Karte Äthiopien englisch

ዮኃንስ በ 11 ዓመቱ ከኢትዮጵያ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ሄዶ ፤ ከ 15 ዓመት ቆይታ በኋላ ነው ወደ ኢትዮጵያ በፊልም ኢንዱስትሪው ለመሳተፍ ከ 9 ወር በፊት የተመለሰው ። የሰዎች እውቀት እንደሚመለከቱት የመገናኛ ብዙኃን ይወሰናል ይላል።

ሃና ሀሳባችንን የሚጋሩ እና ድጋፍ የሚሰጡን በርካታ ሰዎች አግኝተናል ትላለች ።በተለያየ ሀገር የሚኖሩት ወጣቶችም የጉዞዋቸውን ወጪ መሸፈን የሚችሉበትን መላ አግኝተዋል። ሃና እና የሀሳብ አጋሮቿ ፤ ተረት ተረት ያሉትን ፕሮጀክት ዕውን ለማድረግ የእያንዳንዳቸውን እውቀት ተጠቅመው መተግበር ይፈልጋሉ።

ስለ ኢትዮጵያን ስላልተነገሩ ታሪኳ እና ሌላኛው ገፅታዋ፤ እንደ ተረት መንገር እንፈልጋለን በማለት ቆርጠው ከተነሱት ስድስት ወጣቶች መካከል ፤ ከሃና ሰለሞን እና ዮኃንስ በላይ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በድምፅ ያገኙታል።

ልደት አበበ

ነጋሽ መሀመድ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች