ተላላፊ በሽታዎች በኢትዮጵያ | ኢትዮጵያ | DW | 31.03.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ተላላፊ በሽታዎች በኢትዮጵያ

የየአካባቢዉ ነዋሪዎችና አንዳድ የዜና ምንጮች «ኮሌራ» የሚሉት በሽታ አንዳድ አካባቢዎች በርካታ ሰዉ ገድሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ለበሽታዉ አጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት የሚለዉን ሥም ነዉ የመረጠዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:56
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:56 ደቂቃ

ተላላፊ በሽታዎች

ኢትዮጵያ ዉስጥ በደቡብ፤ በኦሮሚያ እና በሶማሌ መስተዳድር የተዛመተዉ የተቅማጥና ትዉከት በሽታ የሰዉ ሕይወት ማጥፋቱ ተዘገበ። የየአካባቢዉ ነዋሪዎችና አንዳድ የዜና ምንጮች «ኮሌራ» የሚሉት በሽታ አንዳድ አካባቢዎች በርካታ ሰዉ ገድሏል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ለበሽታዉ አጣዳፊ ተቅማጥና ትዉከት (አተት) የሚለዉን ሥም ነዉ የመረጠዉ። የጤና ጥበቃ ሚንስቴር እንዳስታወቀዉ በድርቁ እና በንፅሕና ጉድለት ምክንያት ከተቅማጥና ትዉከቱ በተጨማሪ የማጅራት ግትር (ሜኔን ጃይትስ) በሽታም በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል። በበሽታዉ ሥለሞቱ ወይም ሥለታመሙ ሰዎች ብዛት ግን በግልፅ የተነገረ ነገር የለም። የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic