ቮልስቫገን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተፈራረመ | ኢትዮጵያ | DW | 28.01.2019
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

ኢትዮጵያ

ቮልስቫገን ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተፈራረመ

ቮልስቫገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ስምምነት ተፈራረመ። ምምነቱ በርካታ የጀርመን ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ ይስባል ተብሎ ይጠበቃል። 

 

የጀርመኑ የመኪና አምራች ግዙፍ ኩባንያ ቮልስቫገን ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ። ኩባንያው ይህን የመግባብያ ስምምነት ሲፈራረም በኢትዮጵያ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ለማቋቋም ያስችላል ተብሎአል። ስምምነቱን የተፈራረሙት የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ አበባ አበባዬሁ እና በደቡብ አፍሪካ የቮልስቫገን ዋና ሥራ አስኪያጅ ቶማስ ሼፈር ናቸዉ።

የመግባብያ ስምምነቱ ሲፈረም ኢትዮጵያን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር እና የኢትዮጵያ የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ተገኝተዋል። የጀርመኑ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ቫልተር ወደኢትዮጵያ ሲጓዙ የጀርመን ባለወረቶችንና የኤኮኖሚ ጉዳይ ባለሞያዎችን ይዘዉ ነዉ። ስምምነቱ በርካታ የጀርመን ኩባንያዎችን ወደ ኢትዮጵያ ይስባል ተብሎ ይጠበቃል። 


አዜብ ታደሰ 

ተዛማጅ ዘገባዎች