ቦኮሃራም ያፈናቀላቸው ናይጀሪያውያን ችግር | አፍሪቃ | DW | 14.07.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ቦኮሃራም ያፈናቀላቸው ናይጀሪያውያን ችግር

ምሥራቅ ናይጀሪያ ውስጥ በሚገኘው በባማ የስደተኞች መጠለያ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ወደ 200 የሚጠጉ ሰዎች በምግብ እጥረት መሞታቸውን ድንበር የለሹ የሐኪሞች ድርጅት በፈረንሳይኛው ምህፃር MSF ከሁለት ሳምንት በፊት አስታውቋል ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:03

ቦኮሃራም ያፈናቀላቸው ናይጀሪያውያን ችግር


በምግብ እጥረት ከሞቱት መካከል አብዛኛዎቹ ህጻናት ናቸው ። ይህን መሰሉ ችግር የደረሰው በባማው መጠለያ ጣቢያ ብቻ አይደለም ።አሸባሪውን ፅንፈኛ ቡድን ቦኮሃራምን የሸሹ ሰዎች በሚገኙባቸው በሌሎች መጠለያዎች ጭምር እንጂ ።የዶቼቬለው የንስ ቦርሸርስ ቦኮሃራምን ሸሽተው በየቦታው የተጠለሉ ሰዎች የሚደርስባቸውን ችግር ያስቃኘናል ።ለቅንብሩ ኂሩት መለሰ

የናይጀሪያው ፕሬዝዳንት ሙሃማዱ ቡሃሪ የድንበር የለሹን የሐኪሞች ድርጅት የMSF ን ዘገባ እንደሰሙ በእጅጉ ተቆጥተው ነበር ። ለነገሩ ጉዳዩን የናይጀሪያ መገናኛ ብዙሃንም ሲዘግቡት ቆይተዋል ።ያም ሆኖ ከMSF ዘገባ በኋላ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው ነበር ።በውጤቱም በስደተኞች መጠለያዎች የምግብ ችግር እንዳለ ነው የተገለፀው ።በመጨረሻም የናይጀሪያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር እንዳስረዱት ፕሬዝዳንቱ አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ አዘዋል ።
«ፕሬዝዳንቱ ጉዳዩ አሳስቧቸዋል ። ለኤቦላ እንዳደረግነው ዓይነት አንድ የፈጣን ጣልቃ ገብ ኃይል ቡድን እንድናቋቁም ይፈልጋሉ ።
ይህ ፈጣን ጣልቃ ገብ ኃይል ሐኪሞችን ፣ ግብረ ሰናይ ድርጅቶችን እና የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን ያካትታል ። በተለይ በቦርኖ ግዛት ያሉት ስደተኞች የሚገኙበት ሁኔታ አሳሳቢ ነው ።የናይጀሪያ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አድዋሌ በተለይ በምግብ እጥረት የተጠቁትን ስደተኞች ለመታደግ እቅድ መውጣቱን ተናግረዋል ።
«ከመካከለኛ አንስቶ በከባድ የምግብ እጥረት ለሚሰቃዩት ወደ 600 ሺህ ለሚጠጉ ህጻናት እቅድ አውጥተናል ።ከሚገኙበት አደገኛ ሁኔታ እንዲላቀቁ በተለይ ውሐና እና የተዘጋጀ ምግብ በአስቸኳይ ሊቀርብላቸው ይገባል ። »
የተመድ በተለይ በሰሜን ምሥራቅ ናይጀሪያ ቦኮሃራም በሚያደርሰው ጥቃት ምክንያት ከመኖሪያቸው መፈናቀል ግድ


የሆነባቸው ሰዎች የሚገኙበት ሁኔታ ትኩረት እንዲሰጠው ሲሞክር ቆይቷል ።በምህፃሩ AOA የተባለው ግብረሰናይ ድርጅትም ይህን ሲያሳስቡ ከከረሙት ድርጅቶች አንዱ ነው ። የድርጅቱ ሃላፊ አዮዳ አላኪጃ እንደሚሉት ሁኔታውን አሳሳቢ ነው ።
«ከሚያስፈልገን ገንዘብ 22 በመቶው ብቻ እንዳለ ነው የሚነገረን ።ብዙ መሥራት አለብን ።በአንድ ሰዓት ውስጥ 5 ልጆችን ልናጣ እንችላለን ።የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ተቅማጥ ልዩ ልዩ ኢንፌክሽኖች በባማው መጠለያ ያሉ አሳሳቢ የጤና ችግሮች ናቸው ።የንጽህና አጠባበቅ ችግር አለ፣ እዚያ የሚገኙ ወደ 24 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች እዚያ ለሚገኙ ሰዎች በቂ ምግብ የለም ።አንዲት እናት በመጠለያው ስለደረሰው የህጻናት ሞት ለናይጀሪያ ጋዜጠኞች ተናግራለች ።
«አዎ መጠለያው ውስጥ ብዙ ህጽናት ነበሩ ።ብዙዎቹም በረሃብ ምክንያት ሞተዋል ።ሆኖም አሁን እንደ እድል ሆኖ ህጻናቱን

የቦርኖ ዋና ከተማ ማይዱግሪ የሚገኝ ሆስፒታል መews,ድ ጀምረናል።»
የማይዱግሪ ሆስፒታል አቅም ውስን በመሆኑ ሁኔታው አስቸጋሪ ነው ።ማይዱግሪን ከኢህ ቀደም የጎበኙት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሳህል አካባቢ ሃገራት ሰብዓዊ እርዳታዎች አስተባባሪ ላንዘር እዚያ ያለውን ሁኔታ ያብራራሉ
«ቀደም ሲል ከተማው ወደ አንድ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች መኖሪያ ነበር ።አሁን ነዋሪው 2 ነጥብ 6 ሚሊዮን ደርሷል ።በቅርብ ወራት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ የሚሆኑ ሰዎች ቦኮሃራምን ሸሽተው ማይዱግሪ ገብተዋል ።»
የእርዳታ ድርጅቶች እንደሚሉት ቦኮሃራም ከየመንደሮቻቸው ካፈናቀላቸው ሰዎች ውስጥ 8 በመቶው ብቻ ናቸው በመጠለያዎች ውስጥ ያሉት አብዛኛዎቹ ማይዱግሪም ውስጥ ሆነ በሌሎች ስፍራዎች በሚገኙ ዘመዶቻቸው ጋ ነው የተጠጉት ።ለመጠለያ ጣቢያዎቹ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የናይጀሪያ መንግሥት አስቸኳይ እርዳታ ለማቅረብ እየሞከረ ነው ።


ኂሩት መለሰ

አዜብ ታደሰ

Audios and videos on the topic