ቦኮሃራም ያገታቸው ልጃገረዶች የሚለቀቁበት ተስፋ | አፍሪቃ | DW | 20.10.2014
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አፍሪቃ

ቦኮሃራም ያገታቸው ልጃገረዶች የሚለቀቁበት ተስፋ

አክራሪው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን ቦኮሃራም ያገታቸው ከ200 የሚበልጡ ልጃገረድ ተማሪዎችን ይፈታ ይሆን?የናይጄሪያ መንግሥትና ቦኮሃራም የተኩስ አቁም ለማድረግ መስማማታቸው ከተሰማ ካለፈው ዓርብ አንስቶ ትልቅ ተስፋ ተጥሎ ነበር። ይሁንና በሳምንቱ መጨረሻ በመካሄድ ላይ ያሉት ጥቃቶች ተስፋውን የሚያመናምኑ ናቸው።

አክራሪውእስላማዊታጣቂቡድንቦኮሃራም ከ200 የሚበልጡ ልጃገረድተማሪዎችን ካገተ እንሆ ስድስት ወራት ተቆጠሩ። ተማሪዎቹ በአማፂው ቡድን ታግተው የተወሰዱት ሰሜን ምስራቅ ከምትገኘው ትንሽ ከተማ ከቺቦክ ነበር። የታጋቾቹ ጉዳይ ለረዥም ጊዜ መፍትሄ ሳያገኝ ቢቆይም፤ ሰሞኑን ከናይጄሪያ መንግሥት የተሰማው ዜና ልጃገረዶቹ በቅርቡ ነፃ እንደሚሆኑ ያመላክት ነበር። የመንግሥት ቃል አቀባይ ማይክ ኦሜሪ ዓርብ ዕለት ለዶይቼ ቬለ የሀውሳ ክፍልእንዳረጋገጡት፤ መንግሥታቸውና የቦኮ ሀራም ተወካዮች ጎረቤት ሀገር ቻድ ተገናኝተው የተኩስ አቁም ደምብ ደርሰዋል። ኦሜሪ እንደገለፁት ፣ የቺቦክ ልጃገረዶች በቅርቡ ወደ ቤተሰብ እና ዘመዶቻቸው ይመለሳሉ። የሁለቱን ቡድናት የተኩስ አቁም እንዲሁ የፕሬዚዳንት ጉድላክ ጆናታን ታማኝ ሀሳን ቱኩር አረጋግጠዋል፤ « በቅርቡ የተወሰነ የተሳካ ውጤት እንደሚገኝ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ። ለምሳሌ ቻይናውያኑን፣ የካሜሩንን የኮሎፋታን መሪን እና የካሜሩን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ባልተቤትን እንደሚፈቱ ቃል ገብተውልን ነበር፣ እንዳሉትም፣ ታጋቾቹን ለቀዋል። ይህ በጎ ፈቃደኝነታቸውን ያሳየ ምልክት ነው። ውዝግቡንም በድርድር ለማብቃት ዝግጁ መሆናቸውን የሚጠቁም ምልክት ነው።»

Vater des Chibok-Mädchens

ልጆቻቸው የታገቱባቸው አባት

ቱኩር ውዝግቡ ማብቂያ ይኖረዋል የሚል እምነት ቢኖራቸውም የታገቱት ልጃገረዶች መለቀቅን በሚመለከት አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበዋል። የተኩስ አቁም ስምምነት ዜና ግን ለታጋቾቹ ቤተሰቦች ተስፋ ሰጪ ነበር። ምክንያቱም ፣ ዓማፂው ቡድን ቦኮ ሀራም ያገተባቸውን ሁለት ልጆቻቸውን መፈታት በተስፋ የሚጠባበቁት አባት ማላም አሊ እንደሚያምኑት፣ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ከተደረሰ ፤ በሰሜን ናይጄሪያ የቀጠለው የኃይል ርምጃ ያበቃል ።« ሁለት ሴት ልጆች አሉኝ። ትምህርታቸውን ሊያጠናቅቁ ተቃርበው ነበር። የመታገታቸውን ዜና ስሰማ እጅግ ነበር የደነገጥኩት። ልጆቼ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ስል ትንሿን መሬቴን ሁሉ ሸጬ ነበር።»

ማላም አሊ ልጆቻቸው ከታገቱ በኋላ ስለሚገኙበት ሁኔታ ምንም አያውቁም። የአባትየው ስጋት የልጆቻቸው በሰላም መመለስ ብቻ ሳይሆን ስምምነቱ ተጥሶ ጦርነት እንደገና እንዳይከፈት የሚልም ነው። ታጋቾቹ ልጃገረዶች ነገ ማክሰኞ ይለቀቃሉ ተብሎ የተሰማው ዜና በርግጥ ገሀድ መሆን አለመሆኑ አሁንም ብዙ እንዳጠራጠረ ይገኛል።

የናይጄሪያ ፌደራል መንግሥት ባለፉት ጊዜያት ዓመቴታ የሚጣልበት አልነበረም። በይፋ hወጡ በርካታ አሳሳች መረጃዎች ነበሩ። ስለዚህ መንግሥት የሚለውን ማመን ትንሽ ይከብዳል። ልጃገረዶቹን በአይናችን እስካላየን ድረስ፤ምንም ነገር አናምንም።» ይላሉ የሚሲ ራንሰም ኩቲ ፤ ለልጃገረዶቹ መለቀቅ አደባባይ በመውጣት ከሚታገሉት ናይጄሪያውያን አንዷ ።

ፊሊፕ ሳንደር / ልደት አበበ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic