ቦኩ ሐራምና ዩናይትድ ስቴትስ | ዓለም | DW | 06.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ቦኩ ሐራምና ዩናይትድ ስቴትስ

ፕሬዝዳንት ኦባማ ከዚሕ ቀደም እንደተናገሩት ፀረ-ሽብር ዘመቻዉ ዉጤታማ እንዲሆን ከፈለጉ ዘመቻዉን በሌላ መልክ መቀጠል፥ የቤት-ሥራቸዉን በተገቢዉ መንገድ መዉጣት ይገባቸዋል----በመካከለኛዉ ምሥራቅ ለፍልስጤሞች ጥያቄ ተገቢዉን መልስ የሚሰጥ መርሕን ገቢር ማድረግ አለባቸዉ።

WASHINGTON, DC - MAY 23: U.S. President Barack Obama speaks at the National Defense University May 23, 2013 in Washington, DC. Obama used the speech to outline and justify his administration's counterterrorism policy, including increased cooperation with Congress on matters of national security, added transparency regarding the use of drones, and a review of current threats facing the United States. (Photo by Win McNamee/Getty Images)

ኦባማ
ዩናይትድ ስቴትስ በአሸባሪነት የምንትወነጅላቸዉ የምዕራብ አፍሪቃ ቡድናት መሪዎች ያሉበትን ለሚጠቁም ወይም ለሚይዝ በድምሩ ሃያ-ሠወስት ሚሊዮን ዶላር እንደምትሸልም ሰሞኑን አዉጃለች። የዶቸ ቬለዉ ቶማስ መሽ እንደታዘበዉ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣት ይሕን ያወጁት ለተቀረዉ ዓለም ሁለት ነገር ለማሳያት አልመዉ ነዉ።የምዕራብ አፍሪቃ አሸባሪ ቡድናት ለዓለም አስጊ መሆናቸዉ እናዉቃለን ለማለት-አንድ።የአሸባሪ ቡድናቱ መሪዎች እስኪያዙ ድረስ «ልናድናቸዉ» ቆርጠናል-ሁለት።

ትልቁ አደጋ ግን መሽ እንደሚለዉ የዋሽግተኖች አላማ ለምዕራብ አፍሪቃ ፍፁም ተቃራኒ መልዕክት ማስተላለፉ ነዉ።ምክንያቱ እራሷ አሜሪካ ናት።ፕሬዝዳት ባራክ ኦቦማ ባለፈዉ ግንቦት አስራ-አምስት ባደረጉት ንግግር «ፀረ-አሸባሪዎቹ ጦርነት» ማብቃቱን አስታዉቀዉ፥ ፀረ-ሽብሩ ዘመቻ በወታደራዊ ሐይል ብቻ ለድል እንደማይበቃ አስታዉቀዉ ነበር።

Nigerian President Goodluck Jonathan speaks during a nationwide live broadcast on the state television on May 14, 2013. President Goodluck Jonathan has declared state of emergency in the nation's troubled northeast states of Yobe, Borno and Adamawa, where Islamic extremists now control some of the country's villages and towns, promising to send more troops to fight what is now an open rebellion. AFPPHOTO/PIUS UTOMI EKPEI (Photo credit should read PIUS UTOMI EKPEI/AFP/Getty Images)

ጆናታንኦባማ በዚሕ አላበቁም።የኹዋንታናሞ ማጎሪያ ጣቢያን መዝጋት እንደሚሹ በድጋሚ ገልጠዋል። ፓኪስታን ዉስጥ መሽገዋል የሚባሉ ተጠርጣሪ አሸባሪዎችን ለመግደል ድሮን በተሰኙት የሰዉ አልባ አዉሮፕላኖች የሚደረገዉን ዘመቻ ዉጤታማነት መጠራጠራቸዉን አስታዉቀዉም ነበር።ይሕ ሁሉ ተዳምሮ መግለጫዉ፥ ዩናይትድ ስቴትስ አሸባሪዎችን በርዕዮተ-ዓለሙ መስክ ልትፋለም የመወሰኗ ምልክት ነዉ የሚል እምነት፥ ተስፋም ፈንጥቆ ነበር።

የሰሞኑ አዋጅ በብዙ አፍሪቃዉያን በጣሙምን በምዕራብ አፍሪቃ ሙስሊሞች ዘንድ የዩናይትድ ስቴትስ መሪዎች ቃል ከድርጊታቸዉ ይቃረናል የሚል እምነት ነዉ-ያሳደረዉ።ናይጄሪያ ቀዳሚዋ አብነት ናት።የአሜሪካ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር በቅርቡ ባወጀዉ መሠረት ከፍተኛዉ ገንዘብ የሚሸለመዉ ቦኩ ሐራም የተሰኘዉን የናጄሪያ አሸባሪ ቡድን መሪ አቡበከር ሼኩን ለሚጠቁም ነዉ።ሰባት ሚሊዮን ዶላር።

The interior of an unoccupied communal cellblock is seen at Camp VI, a prison used to house detainees at the U.S. Naval Base at Guantanamo Bay in this March 5, 2013 file photo. It's been dubbed the most expensive prison on Earth and President Barack Obama cited the cost this week as one of many reasons to shut down the detention center at Guantanamo Bay, which burns through some $900,000 per prisoner annually. REUTERS/Bob Strong/Files (CUBA - Tags: CRIME LAW MILITARY POLITICS)

ኹዋንታናሞ

ቦኩ ሐራም የሚንቀሳቀስበት የሰሜናዊ ናይጄሪያ ነዋሪዎች የመጀመሪያ አፀፋ ዋሽግተን በሐገራችን የዉስጥ ጉዳይ ጣልቃ ትገባለች የሚል ነዉ።የሰሜን ናጄሪያ ነዋሪዎች አሜሪካን ይጠላሉ።የዚያ አካባቢ ተወላጆችን ለሚጠቁም ወይም ለሚይዝ ገንዘብ እንሸልማለን መባሉ መሽ እንደታዘበዉ የወለፊድ ይባርቃል።

በቅርቡ በቦኩ ሐራም ላይ ሰፊ ወታደራዊ ዘመቻ ለከፈተዉ ለአቡጃ መንግሥትም ጉንጩን በጥፊ ከመምታት የሚቆጠር ነዉ።የፕሬዝዳት ጉድላክ ጆናታን መንግሥት በሰሜናዊ ናጄሪያ ግዛቶች የከፈተዉ ዘመቻ የሚፈለገዉን ዉጤት ማምጣቱን ብዙዎች ይጠራጠራሉ።ጦሩ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚያደርሰዉን ጉዳት፥ በመዘመቻዉ ሰበብ የሰዎች እንቅስቃሴ መታቀቡን፥ የሥልክ መስመሮች መቋረጣቸዉን ብዙዎች ይቃወሙታል።

ፕሬዝዳንት ጆናታን ከአጠራጣሪ ዘመቻ፥ ከሕዝቡም ቅሬታ «የወንድ መዉጫ» ለማግኘት የሰሜናዊ ናጄሪያ ታላላቅ ሰዎች ከቦኩ ሐራም ጋር እንዲደራደሩ ሙሉ ዉክልና ሰጥተዋቸዋል።በዚሕ መሐል ዋሽግተን የአሸባሪ መሪዎችን ለሚጠቁም ገንዘብ እሸልማለሁ ማለቷ ለአቡጃዎች «እኛ በሌለንበት እናንተ ምንም ማድረግ አትችሉም» የሚል መልዕክት ነዉ-የሚያስተላልፈዉ።የጆናታን መንግሥት የዋሽግተኖችን አቋም ቢጋራ ደግሞ ከሐገሩ ሕዝብ የሚነሳዉን ጥያቄ ማስተናገድ ግድ አለበት።

This picture taken on April 30, 2013 shows a Nigerian soldier, part of the 'Operation Flush' patrolling in the remote northeast town of Baga, Borno State. Nigeria's military said on May 16, 2013 that it was ready to launch air strikes against Boko Haram Islamists as several thousand troops moved to the remote northeast to retake territory seized by the insurgents. AFP PHOTO/PIUS UTOMI EKPEI (Photo credit should read PIUS UTOMI EKPEI/AFP/Getty Images)

የናጄሪያ ጦር ዘመቻየቦኮ ሐራም መሪዎችን በገንዘብ አስይዞ አሸባሪዉን ቡድን ማጥፋት ከተቻለ የአሜሪካኖች ገንዘብ መጠበቅ ለምን አስፈለገ-አይነቱን ጥያቄ።በመሠረቱ ፕሬዝዳት ጆናታን አሜሪካኖች የመደቡትን ያሕል ገንዘብ ለማዉጣት ከመንግሥት በጀት መቀነስ አያስፈልጋቸዉም።ጆናታን በሙስና የተዘፈቁ ባለሥልጣኖቻቸዉ ከሚዘርፉት ገንዘብ ጥቂቱን ቢያስመልሱ አሜሪካኖች የመደቡትን ገንዘብ ባጭር ጊዜ እና በቀላሉ ማግኘት አይገዳቸዉም።

በዚሕም ብሎ በዚያ ፕሬዝዳንት ኦባማ ከዚሕ ቀደም እንደተናገሩት ፀረ-ሽብር ዘመቻዉ ዉጤታማ እንዲሆን ከፈለጉ ዘመቻዉን በሌላ መልክ መቀጠል፥ የቤት-ሥራቸዉን በተገቢዉ መንገድ መዉጣት ይገባቸዋል።ሠብአዊ መብት የሚጣስበትን የኹዋንታናሞ ማጎሪያ ጣቢያን መዝጋት።ፓኪስታን ዉስጥ በርካታ የዋሕ ሰላማዊ ሰዎችን የሚፈጀዉን የድሮን ድብደባን ማቆም እና በመካከለኛዉ ምሥራቅ ለፍልስጤሞች ጥያቄ ተገቢዉን መልስ የሚሰጥ መርሕን ገቢር ማድረግ አለባቸዉ።ፅንፈኞች በአሜሪካ ላይ ጥላቻና ቁሮሾን ለመንዘንዛት መሠረት ከሚሆኑት ዋነኞቹ እነዚሕ ናቸዉና፥-ቶማስ መሽ እንደ ታዘበዉ።

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic