ቦን፤ DW ቱኒዚያዊቱን የኢንተርኔት አምደኛ ሸለመ | ዓለም | DW | 14.04.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ቦን፤ DW ቱኒዚያዊቱን የኢንተርኔት አምደኛ ሸለመ

«ቱኒሲያዊቷ ልጃገረድ፣» የተሰኘው የኢንተርኔት የጽሑፍ ዓምድ( BLOG) የዘንድሮውን የ DW 7ኛ ዓለም አቀፍ ሽልማት አሸነፈ።

default

ሊና ቤን ምሄኒ

በኢንተርኔት በተካሄደ የድምፅ አሰጣጥ ሥነ-ሥርዓት፣ ከ 90,000 በላይ ሰዎች ተሳትፈዋል። የተጠቀሰው ድረ ገጽ ዓምደኛ ሊና ቤን ምሄኒ ትባላለች። በቱኒስ ዩኒቨርስቲ አስተማሪ ናት። ስለ ቱኒሲያ የፖለቲካና ማኅበራዊ ኑሮ ለብዙ ዓመታት በፈረንሳይኛ ፤ እንግሊዝኛና ዐረብኛ ስትጽፍ ቆይታለች። በቀድሞው ፈላጭ ቆራጭ መሪ ቤን አሊ ሥር በነበረችው ቱኒሲያ፤ ስለጭቆና፤ ስለጽሑፍ ቅድመ- ምርምራ፣ ሰፊ ማብራሪያ ታቀርብ ነበር። ባለፈው ታኅሳስና ጥር፤ ሲዲ ቡዚድና ካሰሪን ወደተባሉት ከተሞች በመጓዝም፤ ይደርግ የነበረውን ጭቆናና የኃይል እርምጃ አስመልክታ ዘግባለች። በየስሚን አብዮት ለውጥ ከመጣ ወዲህም ምሄኒ፤ አገሪቱ ወደ ዴሞክራሲ ለመሸጋገር የገጠሟትን ደንቃራዎች እያነሳች ጽፋለች። የኢንተርኔት የጽሑፍ ዓምድዋ ቱኒሲያ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በመታገዱ በውጭ ሀገራት ብቻ ነበረ የሚነበበው። የዶጨ የፕሮ ጋራሞች የበላይ ኀላፊ ክርስቲያን ግራምሽ እንዳሉት የዘንድሮው ውድድር ፤ የመገናኛ ብዙኀንና የሐሳብ ነጻነት በተገታባቸው አገሮች ፤ ሰብአዊ መብት የቱን ያህል ዐቢይ ግምት የተሰጠው መሆኑን እንዳሳዬ ገልጸዋል።