ቦምብ ለማፈንዳት በመሞከር የተያዘው ሶማሊያዊ አሜሪካዊ | ዓለም | DW | 29.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ቦምብ ለማፈንዳት በመሞከር የተያዘው ሶማሊያዊ አሜሪካዊ

በአሜሪካንዋ የኦሪገን ግዛት ውስጥ በርካታ ህዝብ በተሰበሰበበት ዝግጅት ላይ ቦምብ ለማፈንዳት በሞመከር ባለፈው አርብ የተያዘው ሶማሊያዊ አሜሪካዊ ዛሬ ለፍርድ ይቀርባል ።

default

ኦስማን ማህሙድ

ወጣቱ በጅሀድ ለመሳተፍ ባለፈው ዓመት ፓኪስታን መሄድ ስለ ሚችልበት ሁኔታ እዚያ ከሚገኝ አንድ ግለሰብ ጋር በኢሜል መልዕክት ይለዋወጥ እንደነበር ለፍርድ ቤት የቀረቡ መረጃዎች ያስረዳሉ ። የሚኒሶታው የማካሊስታር ዩኒቨርስቲ ፕሮፌሰር አህመድ ሳማታር ለዶይቼቬለ እንደተናገሩት ሶማሊያዊ አሜሪካውያን ስማቸው ከሽብር ጋር ተያይዞ በተደጋጋሚ መነሳቱ በሶማሊያ አሜሪካዋን ላይ አሉታዊ ጫና ያሳድራል ። አበበ ፈለቀ ከዋሽግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ