ብክለትና ልማት | ጤና እና አካባቢ | DW | 26.02.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ብክለትና ልማት

ልማት ሲታሰብ በብዙ ዘርፍ ቀድሞ የሚታየዉ ለአገር የሚያስገኘዉ የዉጪ ምንዛሪ፤ ለህብረተሰቡ የሚሰጠዉ ጥቅምና፤ የመሳሰሉት አዎንታዊ ጎኖች መሆኑ ግልፅ ነዉ።ለልማት እድገትና ለዉጪ ምንዛሪ ገቢ ሲታለም በሂደቱ ለተፈጥሮ ጥበቃ ትኩረት ቢሰጥ ከኋላ ፀፀት መዳን ይቻላል።

.........ከዛሬዉ ይታሰብበት

.........ከዛሬዉ ይታሰብበት

በተለያዩ ዘርፎች ለልማት በሚደረገዉ ርብርብ ስራ ላይ የሚዉሉ ተፈጥሯዊ ያልሆኑ የሂደቱ አጫፋሪዎች፤ ለምሳሌ በእርሻዉ ዘርፍ ብናይ ማዳበሪያና ተባይ ማጥፊያዉ ሁሉ የኋላ ኋላ አሉታዊ ጫናቸዉን በአካባቢ ላይ ጥለዉ ማለፋቸዉ አይቀርም።