ብቻቸውን ተሰዳጅ ሕጻናት በአዉሮጳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 09.02.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ብቻቸውን ተሰዳጅ ሕጻናት በአዉሮጳ

ግጭትና ጦርነት በሚሸሽ በአፍሪቃና በመካከለኛዉ ምስራቅ ዉስጥ ከሚገኙ ሃገራት በርካታ አዳጊ ሕጻናትና ወጣቶች ከቤተሰቦቻቸዉ ተነጥለዉ ወደ አዉሮጳ ይሰደዳሉ። እነዚህ ያለ ቤተሰብና ያለምንም ተከታይ ወደ አዉሮጳ የሚሰደዱት ሕጻናት በቀላሉ ለወንጀል ነክ ብዝበዛ ተጋላጭ ናቸዉ ሲሉ አንዲት የአዉሮጳ ሕብረት ኮሚሽን የሕግ ጉዳይ ተጠሪ አስጠንቅቀዋል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 02:55

ታዳጊ ስደተኞች በአዉሮጳ

 

ለአካለ መጠን ያልደረሱ የ 17 የ 15 እንዲሁም የ10 ዓመት ታዳጊ ሕጻናት ናቸዉ በቅርቡ በአንድ ጭነት መኪና  ዉስጥ ተደብቀዉ የተገኙት ። የከባድ መኪና አሽከርካሪዉ ቤንዚን ለመቅዳት ቤንዚን ማደያ ቆሞ ሳለ ነዉ ድንገት መኪና ዉስጥ ተደብቀዉ ያገኛቸዉ። ሕጻናቱ እንደተናገሩት የመጡት ከአፍጋኒስታ ሲሆን በቀጣይ ወደ ጀርመን አልያም ወደ ቤልጂየም መሄድ ይፈልጋሉ። እነዚህ ብቻቸውን የተሰደዱት ሦስት ሕጻናት ከበርካታ ተሰዳጅ  ሕጻናት መካከል ጥቂቶቹ ናቸዉ። በአዉሮጳ ኅብረት ኮሚሽን የሕግ ጉዳዮች ዋና ተጠሪ ቬራ ዩሮቫ እንደተናገሩት በጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓ.ም 100 ሺህ ታዳጊ ሕጻናት ያለምንም ወላጅና ተከታይ ወደ  አዉሮጳ ተሰደዋል።

«ወደ አዉሮጳ ከሚሰደዱ አራት ተገን ጠያቂዎች መካከል አንዱ ታዳጊ ሕጻን አልያም ወጣት ነዉ። ከነዚህ ታዳጊዎች መካከል ደገሞ ገሚሱ ያለምንም ተከታይና ወላጅ የሚመጡ ናቸዉ።»

በሃገራቸዉ በችግርና ጦርነት ሰበብ አዕምሮአቸዉ በጭንቀት የተበረዘዉ እነዚህ ወደ አዉሮጳ የተሰደዱት ታዳጊ ልጆች አዉሮጳ ከገቡ በኅላ ለብቻቸዉ እንዳይጉላሉና ተጨማሪ ጭንቀት ዉስጥ እንዳይገቡ የአዉሮጳ ኅብረት አባላት ሃገራት አንድ ነገር ሊያደርጉ ይገባል ሲሊ ቬራ ዩሮቫ ተናግረዋል።  

ከዚህ በተጨማሪም ሌሎች ችግሮችም አሉ። ሕጻናትና ወጣቶች ለአንድ ወንጀል ድርጊቶች  ብዝበዛ በቀላሉ ተጋላጭ ናቸዉ።»

የአዉሮጳ ፖሊስ ድርጅት ቢሮ «Europol» እንዳስታወቀዉ በአዉሮጳ ቢያንስ 10 ሺህ ለአካለ መጠን ያልደረሱ ታዳጊ ሕጻናት የደረሱበት አይታወቅም ጠፍተዋል። ከጠፉት ሕጻናት መካከል አብዛኞቹ ደግሞ ተገኝተዋል እንደ ብዙዎች ምት ከሆነ ሕጻናቱ የወንጀል ድርጊት በሚፈጽሙ ሰዎች ብዝበዛ ተካሂዶባቸዋል። አንዳንድ ዉስጣዋቂዎች እንደተናገሩት እነዚህ ያለወላጅ አልያም ያለተከታይ ወደ አዉሮጳ የተሰደዱት ሕጻናት እፅን ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ለማዘዋወር አልያም እፅን ለማዘዋወር ለሌሎች ይሰራሉ። ሕጻናቱ ይህን የሚሰሩት ብዙ ገንዘብ ከፍለዉ ወደ አዉሮጳ ለላኩዋቸዉ ቤተዘመዶች ገንዘቡን መመለስ ስላለባቸዉ ነዉ። ከዚህ ሌላ ትዉልድ ሃገራቸዉ የሚገኙትን ወላጆቻቸዉን ወንድም እህቶቻቸዉን ገንዘብ በመላክ መርዳት የሚፈልጉ አሉ።  የአዉሮጳ ህብረት የሕግ ጉዳዮች ተጠሪ ቬራ ዩሮቫ እንደገለፁት የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ለነዚህ ሕጻናት ስደተኞች ምግብና መጠለያን ብቻ ሳይሆን ወደፊት አስተማማኝ ቦታ ላይ እንዲደርሱ ድጋፍ ሊሰጡ ይገባል።

« ሕጻናቱ ለወደፊት አስተማማኝ ሕይወትን የሚቀይሱበት መንገድ ከሌላቸዉ ትዉልዱ ይጠፋል።» የጠፋዉ የስደተኛ ሕጻናት ትዉልድ ሲባል ቋንቋን በትክክል መናገር ሳይናገሩና ጥሩ ስልጠናና ትምህርትን ሳይወስዱ የቀሩ ታዳጊ ሕጻናት በማኅበረሰቡ ዉስጥ ተዋሕዶ ለመኖር አይችሉም ። ይህ ደግሞ ምናልባት ወደ ወንጀለኝነት መንገድን የሚያመራ ተግባር ላይ ሊጥላቸዉ ይችላል። በዚህ ይላሉ ቬራ ዩሮቫ የአዉሮጳ ኅብረት አባል ሃገራት ታዳጊ ለታዳጊ ሕጻናቱ ድጋፍ ከሰጡ የነገን ችግር ዛሬ ቀረፉ ማለት ይሆናል።     

ካሪን ቤኒሽ / አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic