ብርድ፤ ነርቭ እና ሕመም | ጤና እና አካባቢ | DW | 31.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ጤና እና አካባቢ

ብርድ፤ ነርቭ እና ሕመም

አንዳንድ ሰዎች ከሞቃት ስፍራ ወጥተዉ አየር ለመቀበል ሲሞክሩ፤ ወይም በሞቃቸዉ ሰዓት የለበሱትን ሲያወላልቁ፤ አለያም ከሁለት ተቃራኒ አቅጣጫ ንፋስ ከሚመጣበት ስፍራ ተቀምጠዉ ብርድ እንደመታቸዉ ሲናገሩ ይደመጣል። ብርድ መታኝ ሲሉ፤ ወይ ራስ ምታት፤ ወይም ዉጋት ወይም ሳል እያለ የተለያየ የጤና እክል እንዳስከተለባቸዉም ይናገራሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 10:48
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
10:48 ደቂቃ

ብርድ እና ሕመም

የህክምና ባለሙያዎች ስለዚህ ችግር ምን ይላሉ?

«ድራፍት ኢዝ ዴንጀረስ» የሚጋጭ ንፋስ እንበለዉ አደገኛ ነዉ፤ የሚል አጠር ያለ አንድ ጽሑፍ እንዲህ ያስረዳል፤ የሞቃት ወይም የቀዝቃዛ ሰዉነት ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። አንድ ሰዉ ከከፍተኛ ፎቅ ላይ ሆኖ በዉቅያኖስ አቅጣጫ ያለ መስኮቱን እየከፈተ ንፋስ ለመቀበል ሲሞክር በተደጋጋሚ ለራስ ምታት መጋለጡን የሚያትተዉ ይህ ጽሑፍ ሙቀት፣ ወይም ቅዝቃዜን ሰዉነታችንን ለመቋቋም አቅም እንዳለዉ ይጠቁማል።

ግን ደግሞ ይላል ሰዉነት በተዳከመ ወይም የሥራም ሆነ የሌላ ሃሳብ ጫና በበዛበት ጊዜ እንዲያ ያለዉ ንፋስ ሲያጋጥመዉ በቀላሉ ሊጎዳ እንደሚችል ይጠቁማል። ሰዎች ብርድ መታን፣ ወይም ለንፋስ ተጋለጥን ሲሉ እንሰማለን፤ እኛም ሊያጋጥመን ይችላል። ይህ ደግሞ አንዳንዴ ለራስ ምታት ወይም ለጉንፋን ወይም ለሌላ የጤና ችግር መንስኤ ሲሆን ይታያል፤ ይህ እንዴት ነዉ ለሚለዉ የነርቭ ሃኪሙ ዶክተር ተሻገር ደመቀ ማብራሪያ አላቸዉ።

ሥርዓተ ነርቭ ዉስብስ እንደመሆኑ ችግሩም ሆነ የሚታየዉ እንከን በቀላሉ የሚገለጽ አይመስልም። ያም ሆኖ እንዲህ ያለዉ ችግር ሲያጋጥም ይላሉ ዶክተር ተሻገር ወደ ሃኪም ሄዶ ተገቢዉን ምርመራ ማድረግ ነዉ።

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic