ብርቱ የተቃውሞ ሰልፍ በብራዚል፤ | ዓለም | DW | 19.06.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ብርቱ የተቃውሞ ሰልፍ በብራዚል፤

በአሁኑ ጊዜ ከክፍለ ዓለማቱ የተወከሉ የእግር ኳስ ቡድኖችን የ«ኮንፈደሬሽን ዋንጫ» በተሰኘው ውድድር በማስተናገድ ላይ የምትገኘው የከርሞው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ብራዚል ፤ ሰሞኑን በታላቅ ህዝባዊ ሰልፎች በመናጥ ላይ ናት።

ሰልፈኞቹ፤ መንግሥት ለህዝቡ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መገልገያዎችን ችላ ብሎ ለዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ዝግጅት እንዲሁም ለግንባታ ኩባንያዎች ሰፊ ወጪ ያደርጋል በማለት ነው የሚቃወሙት። የብራዚል መንግሥት፤ ሰሞኑን የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ከሚካሄድባቸው 6 ታላላቅ ከተሞች ወደ 5ቱ በዛሬው ዕለት ልዩ የፌደራል ፖሊስ ኃይል እንደሚያሠማራ ተነግሯል። የብራዚል ዓለም አቀፍ የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅነትና የሰልፈኞች ብሶት ቀጥሎ የምንዳስሰው ርእስ ነው

ባለፈው ሰኞ ምሽት፤ በአገሪቱ በመላ 240,000 ህዝብ ነበረ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን የገለጠው። ትናንት ማታም 50,000 ሰዎች፤ በሳዖ ፓውሎ ከተማ መኻል ወደሚገኘው ዋናው ካቴድራል በማምራት ጥያቄዎቻቸውን አሰምተዋል። ከትናንት በስቲያ ፣ ምንም እንኳ፣ ጥቂት ጋጠ ወጦች ከፖሊስ ጋር ግብ -ግብ ለመግጠምና የሱቆችን በሮች ለመሠባበር ተሠማርተው ነበረ ቢባልም፤ አብዛኞቹ የተቃውሞ ሰልፈኞች በማሕበራዊ ኑሮ የገጠማቸውን ችግር፣ የኑሮ ውድነትን መንስዔ በማድረግ ነበረ አደባባይ የወጡት ።

በውጭ ሀገራት የሚገኙ የብራዚል ተወላጆችም በተለይ በሜክሲኮ፤ ፖርቱጋል፤ እስፓኝና ዴንማርክ የሚኖሩት በትናንቱ ዕለት የትብብር የተቃውሞ ሰልፍ አድርገው ነበር።

የብራዚል መንግሥት ይፋ የዓለም የአግር ኳስ ዋንጫ ድረ ገጽም በድብቅ በሚሠሩ የኮምፒዩተር ጠቢባን መሠረዙ ነው የተመለከረው።

የብራዚልን ህዝብ ለቅጽበታዊ ተቃውሞ ያነሣሣው ፤ የመጓጓዣ ዋጋ መጨመር፤ ለዓለም የአግር ኳስ ዋንጫ ዝግጅት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ መደረጉ ነው። ለትምህርትና ለጤና የሚመደበው ገንዘብ አነስተኛ መሆኑም ተመልክቷል። በአጠቃላይ በአገሪቱ ተንሠራፍቷል የተባለው ሙስናም እንዲወገድ ነው ሰልፈኞቹ አበክረው የጠየቁት። ከሰልፈኞቹ መካከል ላይር ፔድሮሳ የተባሉት እንዲህ ያላሉ።

«በሙስና በተዘፈቀችው ብራዚል ነው የምንኖረው።ጤና፤ የሥራ ጉዳይ ፤ ትምህርት ሁሉም ፤ ሁሉም በተሳሳተ መንገድ ነው የሚመራው።»

ራይስ ግላድሰን የተባለው የዩንቨርስቲ ተማሪም እንዲህ ነበረ ያለው።

«ለዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ፣ እንዲሁም ለግንባታ ኩባንያዎች የሚወጣው ይቀነስና ለትምህርት ቤቶች፤ እንዲሁም ለሆስፒታሎች ላቅ ያለ ገንዘብ ይሰጥ!።»

የብራዚል መንግሥት፣ 13,3 ቢሊዮን ዶላር ለእስታዲዮሞች ግንባታ፣ ለአኤሮፕላን ማረፊያ ጣቢያዎች ማደሻ እንዲሁም ለሌሎች ከዓለም የአግር ኳስ ዋንጫ ጋር ለተያያዙ ፕሮጀክቶች መድቧል። እ ጎ አ በ 1916 በዚያው በብራዚል ፣ በሪዮ ለሚካሄደው ኦሊምፒክስ ውድድርም 12 ቢሊዮን ዶላር ነው የተመደበው።

ቀድሞ የግራ ፈለግ ተከታይ ደፈጣ ተዋጊ እንደነበሩ የተነገረላቸውና ወደ እሥር ቤት ተወርውረው ፤ እ ጎ አ ከ 1964 እስከ 1985 በቆየው አምባገነናዊ አገዛዝ ቁም ስቅል የሚያሳይ የግፍ እርምጃ የተወሰደባቸው ፤ ያሁኗ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ፣ ወ/ሮ ዲልማ ሩሴፍ፣ የህዝቡን ችግር እንደሚገነዘቡ ቢገልጹም በሳዖ ፓውሎ የታየው ሁከትና አፍራሽ ተግባር በቸልታ የሚታለፍ አይደለም ነው ያሉት።

«የሁከቱን ተግባር በጥብቅ እናወግዛለን፤ እንደመንግሥትና ኅብረተሰብ፤ ማንኛውም የሁከት ተግባር ፣ አውዳሚና አሣፋሪ ብቻ ሳይሆን ፣ የኃይል እርምጃ ይበልጥ የኃይል እርምጃን ነው የሚጋብዘው።»

በአሁኑ ጊዜ ከክፍለ ዓለማቱ የተወከሉ የእግር ኳስ ቡድኖችን የ«ኮንፈደሬሽን ዋንጫ» በተሰኘው ውድድር በማስተናገድ ላይ የምትገኘው የከርሞው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ብራዚል ፤ ሰሞኑን በታላቅ ህዝባዊ ሰልፎች በመናጥ ላይ ናት። ሰልፈኞቹ፤ መንግሥት ለህዝቡ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መገልገያዎችን ችላ ብሎ ለዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ዝግጅት እንዲሁም ለግንባታ

በብራዚል ታላላቅ ከተሞች፣ የሁከቱ ተቀዳሚ ሰበብ የሆነው በአውቶቡስና በትኅተ ምድር ባቡር አገልግሎት ተጠቃሚዎች ከመደበኛው ዋጋ በተጨማሪ 10 ሳንቲም እንዲከፍሉ በመገደዳቸው ነው። አካባባያዊ አስተዳደሮች ቢያንስ በ 4 ከተሞች፤ ጭማሪው እንዲሰረዝ ተስማምተዋል። የከተሞችና የፌደራል ክፍላተ ሀገር አስተደደሮች፤

Dilma Rousseff

ፕሬዚዳንት ዲልማ ሩሴፍ

በአሁኑ ጊዜ ከክፍለ ዓለማቱ የተወከሉ የእግር ኳስ ቡድኖችን የ«ኮንፈደሬሽን ዋንጫ» በተሰኘው ውድድር በማስተናገድ ላይ የምትገኘው የከርሞው የዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር አዘጋጅ ብራዚል ፤ ሰሞኑን በታላቅ ህዝባዊ ሰልፎች በመናጥ ላይ ናት። ሰልፈኞቹ፤ መንግሥት ለህዝቡ የሚያስፈልጉ መሠረታዊ መገልገያዎችን ችላ ብሎ ለዓለም የእግር ኳስ ዋንጫ ዝግጅት እንዲሁም ለግንባታ በሳዖ ፓውሎም የመጓጓዛው ዋጋ ጭማሪ መሠረዙ እንደማይቀር ነው የገለጹት።

ተቃዋሚዎቹ፤ በፕሬዚዳንት ዲልማ ሩሴፍ አስተዳደር ላይ ብርቱ ተቃውሞ በማሰማት ላይ ቢሆኑም ፣ ፕሬዚዳንቷ ምን ዓይነት ተጋባራዊ ምላሽ እንደሚሰጡ አልጠቀሙም።

መንግሥታቸው ፣ አሁን በመካሄድ ላይ ያለው የእግር ኳስ ኮንፈደሬሽን ዋንጫ ውድድር ብቻ ሳይሆን በመጪው ዓመትም የዓለምን የእግር ኳስ ዋንጫ ውድድር ብራዚል ስለምታስተናግድ ፣ እንዲሁም በሰሜኑ ንፍቀ ክበብ ሞቃት ወራት ፤ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንሲስ፣ ሪዮ ደ ጃኔሮንና ገጠሩን ሳዖ ፓውሎን ስለሚጎበኙ፣ የፀጥታ አጠባበቅ ይዞታ ፣ ካሁኑ እጅግ እንዳሳሰበው መግለጹ አልቀረም።

ተክሌ የኋላ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic

ተዛማጅ ዘገባዎች