ብሪታንያ እና የአዉሮጳ ሕብረት አባልነቷ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 17.05.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ብሪታንያ እና የአዉሮጳ ሕብረት አባልነቷ

በቅርቡ በተደረገዉ የከተሞች አስተዳደር ምርጫ የጠቅላይ ሚንስትሩ ወግ አጥባቂ ፓርቲ በርካታ መቀመጫዎችን ማጣቱ፥የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ይበልጥ ማሽቆልቆሉና ከምሥራቅ አዉሮጳ ወደ ብሪታንያ የሚገባዉ ሕዝብ ቁጥር መጨመሩ የአዉሮጳ ሕብረት የብሪታንያን ሉዓላዊነት እየተጋፋ ነዉ የሚሉ ወገኖችን ቅሬታ አጠናክሮቷል

Britain's Prime Minister David Cameron (R) and deputy prime minister Nick Clegg attend the State Opening of Parliament, in the House of Lords at the Palace of Westminster in London May 8, 2013. British Prime Minister David Cameron pledged a fresh clampdown on immigration in the Queen's Speech, seeking to bolster his right-wing credentials against the rise of the UK Independence Party (UKIP). AFP PHOTO/POOL/TOBY MELVILLE (Photo credit should read TOBY MELVILLE/AFP/Getty Images)

ዴቪድ ካሜሩን እና ምክትላቸዉ ኒክ ክሌግ

የብሪታንያ ፖለቲከኞች ሐገራቸዉ የአዉሮጳ ሕብረት አባል እንደሆነች ትቀጠል-አትቀጥል በሚለዉ ሐሳብ ዳግም የገጠሙት ዉዝግብ የጠቅላይ ሚንስትር ዴቪድ ካሜሩንን መንግሥት እየገዘገዘዉ ነዉ።ጠቅላይ ሚንስትሩ ብሪታንያ በሕብረቱ አባልነት መቀጠል-አለመቀጠሏን የሐገሪቱ ሕዝብ እንደ ጎርጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር በ2017 በድምፁ እንደሚወስን ከዚሕ ቀደም አስታዉቀዉ ነበር።በቅርቡ በተደረገዉ የከተሞች አስተዳደር ምርጫ የጠቅላይ ሚንስትሩ ወግ አጥባቂ ፓርቲ በርካታ መቀመጫዎችን ማጣቱ፥የሐገሪቱ ምጣኔ ሐብት ይበልጥ ማሽቆልቆሉና ከምሥራቅ አዉሮጳ ወደ ብሪታንያ የሚገባዉ ሕዝብ ቁጥር መጨመሩ የአዉሮጳ ሕብረት የብሪታንያን ሉዓላዊነት እየተጋፋ ነዉ የሚሉ ወገኖችን ቅሬታ አጠናክሮቷል።በዚሕም ምክንያት የጠቅላይ ሚንስትሩ ፓርቲ ሚንስትሮች እና የምክር ቤት አባላት ሳይቀሩ የካሜሩንን አቋም እየተቃወሙ ነዉ።የለንደኑ ወኪላችን ድልነሳ ጌታነሕን በስልክ አነጋግሬዋለሁ።

ድልነሳ ጌታነሕ

ነጋሽ መሐመድ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic