ብሪታንያ በጥቃት ማግሥት | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 25.05.2017
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages
ማስታወቂያ

አውሮጳ/ጀርመን

ብሪታንያ በጥቃት ማግሥት

ማንቸስተር ብሪታንያ ዉስጥ ሰኞ ዕለት ከደረሰዉ የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት ጋር ግንኙነት አላቸዉ በሚል የተጠረጠሩ ስምንት ሰዎች መያዛቸዉ ተሰምቷል። ከተያዙት መካከል ጥቃቱን አድርሶ ከ22 ሰዎች በላይ ሕይወትን ያጠፋዉ ትዉልደ ሊቢያዊ ታላቅ ወንድም ይገኝበታል።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:02

ለሞቱት የሕሊና ጸሎት በማንቼስተር፤

ጥቃት አድራሹ ራሱን እስላማዊ መንግሥት የሚለዉ ቡድን አባል መሆኑ መረጋገጡን ፖሊስ ጠቁሟል። የብሪታንያ ፖለቲከኞች ለደረሰዉ ጥቃት የፖሊስ በጀት እንዲጨመር ለቀረበዉ ጥያቄ በቶሎ ምላሽ አልሰጡም ያሏቸዉ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቴሬዛ ሜይም ኃላፊነት አለባቸዉ እያሉ ነዉ። ለንደን በታጠቁ ወታደሮች መጠበቅ መጀመሯም ተነግሯል። ከለንደን ዘጋቢያችን ሃና ደምሴ ዘገባ ልካለች።

ሃና ደምሴ

ሸዋዬ ለገሠ

አርያም ተክሌ

Audios and videos on the topic