ብሪታኒያና አዲሱ የስደተኞች ህግ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 27.08.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ብሪታኒያና አዲሱ የስደተኞች ህግ

በእንግሊዝና በዌልስ ግዛቶች ሥራ ላይ ይውላል ተብሎ በሚጠበቀው በአዲሱ ህግ ፣ህገ-ወጥ የሚባሉ የውጭ ዜጎች ከተያዙ የስድስት ወር እሥራት እንደሚጠብቃቸውና እሥራታቸውንም እንደጨረሱ ወደ መጡበት ሃገር እንደሚባረሩ ተገልጿል ።


የብሪታኒያ መንግሥት በሃገሪቱ በህገ ወጥ መንገድ የሚኖሩና ያለ ፈቃድ የሚሰሩ የውጭ ዜጎችን ማሰርና ከብሪታኒያ እንዲባረሩ ማድረግ የሚያስችል አዲስ ህግ ሥራ ላይ እንደሚውል ማሳወቁ እያነጋገረ ነው ። መንግሥት ህጉን የሚያወጣው ወደ ብሪታኒያ በህገ ወጥ መንገድ የሚሰደደው ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ መሆኑን ይናገራል ። የመብት ተሟጋቾች በበኩላቸው መንግሥት የሚያቀርበው ምክንያት ተቀባይነት የለውም ሲሉ ይሟገታሉ ። በእንግሊዝና በዌልስ ግዛቶች ሥራ ላይ ይውላል ተብሎ በሚጠበቀው በአዲሱ ህግ ፣ህገ-ወጥ የሚባሉ የውጭ ዜጎች ከተያዙ የ6 ወር እሥራት እንደሚጠብቃቸውና እሥራታቸውንም እንደጨረሱ ወደ መጡበት ሃገር እንደሚባረሩ ተገልጿል ። ህገ ወጥ የሚባሉትን የሚያሠሩና ቤት የሚያከራዩም ቅጣት እንደሚጠብቃቸው ተነግሯል ።

ድልነሳ ጌታነህ

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

Audios and videos on the topic