ብሔራዊ የመግባባት ጉባኤ ሊጠራ ነዉ | ኢትዮጵያ | DW | 10.07.2018
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ብሔራዊ የመግባባት ጉባኤ ሊጠራ ነዉ

የአምስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች እንደሚሉት ጉባኤዉ ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ ዉጪም ሐገር ዉስጥም ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የሲቢክ ማሕበራት እና የተለያዩ ኃይማኖታዊ ተቋማት የሚካፈሉበት ነዉ

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:51
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:51 ደቂቃ

የብሔራዊ መግባባት ጉባኤ ጥሪ

ኢትዮጵያ ዉስጥ ብሔራዊ የመግባባት እና የእርቅ ጉባኤ ለማድረግ አምስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች በጋራ እየጣሩ መሆኑን አስታወቁ።የአምስቱ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተወካዮች እንደሚሉት ጉባኤዉ ገዢዉ ፓርቲ ኢሕአዴግን ጨምሮ ዉጪም ሐገር ዉስጥም ያሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የሲቢክ ማሕበራት እና የተለያዩ ኃይማኖታዊ ተቋማት የሚካፈሉበት ነዉ።ለጉባኤዉ በሚደረገዉ ዝግጅት እና በራሱ በጉባኤዉ ላይ የኢትዮጵያ ጉዳይ ይመለከተናል የሚሉ በሙሉ እንዲሳተፉ የአምስቱ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጥሪ አድርገዋል።ተወካዮቹ እንደሚሉት ጉባኤዉን እስከ መጪዉ ነሐሴ ወር ድረስ ይደረጋል። 

ጌታቸዉ ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic