ቤጂንግ-የራይስ ጉብኝት | ዜና | DW | 02.07.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዜና

ቤጂንግ-የራይስ ጉብኝት

ቤጂንግ-የራይስ ጉብኝት

default

ራይስ ከዳይ ቢንግ

የዩናይትድ ስቴትሷ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ኮንዳሊሳ ራይስ በቻይና የሚያደርጉትን የሁለት ቀን ጉብኝት ዛሬ ጀምረዋል።ራይስ በዛሬዉ የመጀመሪያ ዕለት ጉብኝታቸዉ መጀመሪያ የሔዱት ባለፈዉ ግንቦት በመሬት መንቀጥቀጥ በርካታ ሕዝብ ወዳለቀባት ሺሹዋን ክፍለ-ግዛት ነበር።ሲሹዋን በመታዉ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ ከሰባ ሺሕ በላይ ሕዝብ አልቋል።አሜሪካዊቷ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር በሐገራቸዉ ሕዝብና መንግሥታቸዉ ሥም ሐዘናቸዉን ገልጠዋል።ራይስ በፖለቲካዉ መስክ ሰሜን ኮሪያ የኒክሌር መርሐ ግብሯን እንድትሰርዝ በተደረገዉ ሥምምነት ገቢራዊነት ላይ ከቻይና ባለሥልጣናት ጋር ይወያያሉ።