1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

6ኛው ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

እሑድ፣ ሰኔ 16 2016

በታዛቢነት የተሳተፉ ከሲቪክ ማህበራት አባላት መካከል አንዱ በሆነው የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ህብረት በአሶሳ ከተማ በተገኙበት ምርጫ ጣቢያ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት የምርጫ ቦርድ ህግን በተከተለ መልኩ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን ጠቁሟል፡፡

https://p.dw.com/p/4hOzP
Äthiopien | Wahl
ምስል Negasa Desalegn/DW

ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል

6ኛው ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማን ጨምሮ በተለያዩ ወረዳዎች ውስጥ ዛሬ ተካሂዷል፡፡ ዛሬ ተዘዋውረን በተመለክናቸው በአሶሳ ከተማ ውስጥ ከተዘጋጁ የድምጽ መስጫ ጣቢያዎች መካከል በአምስት ጣቢያዎች ከጠዋት 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የድምጽ አሰጣጥ ሂደት እየተከናወነ ውሏል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 40 ምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ ምርጫ እንደማይካሄድ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ትናንት በአዲስ አበባ ለመገናኛ ብዙሐን በሰጡት መግለጫ አመልክተዋል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ2013 ዓ.ም በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ በክልሉ ሁለት ዞኖች በጸጥታ ችግር ምክንያት ሳይካሄድ የቆየ ሲሆን በአሶሳ ዞን ደግሞ በድምጽ መስጫ ወረቀት እጥረትና ኮድ ስህተት ምርጫ ሂዴት ተቋርጦ ቀርቷል፡፡ በዛሬው ዕለት አሶሳ ከተማ ጨምሮ በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች 6ኛው ዙር ድጋሚና ቀሪ ምርጫ ተካሂዷል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መራጮች ለምርጫ ተሰልፈው ሲጠባበቁ
በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መራጮች ለምርጫ ተሰልፈው ሲጠባበቁምስል Negasa Desalegn/DW

በአሶሳ ከተማ በተዘጋጁ የምርጫ ጣቢያዎች ከጠዋት 12፡00 ሰዓት አንስቶ የደምፅ አሰጣጥ ሂደት የተጀመረ ሲሆን በአንድ አንድ ጣቢያዎች ረጃጅም ሰልፎች፣ በአንድ አንዱ ጣቢያ ደግሞ እስከ ቀኑ ስድስት ሰዓት ባሉበት ጊዜያዎች አነስተኛ ቁጥር ያለው መራጭ ተመለክተናል፡፡ በአሶሰ ከተማ ውስጥ በተመለክተኳቸው አምስት የሚደርሱ የምርጫ ጣቢያዎች በድምጽ አሰጣጥ ሂዴት የተሳተፉና ያነጋርናቸው መራጮችም ምርጫው በሰላም መካሄዱን ነግረውናል፡፡

ዛሬ በተካሄደው 6ኛ ዙር ምርጫ የተፎካካሪ ፓርቲና የብልጽግና ፓርቲ ተወካዩች ምርጫው አሳተፊና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከጠዋት 12፡00 ጀምሮ መካሄድ መጀመሩን በየፊናቸው አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም በታዛቢነት የተሳተፉ ከሲቪክ ማህበራት አባላት መካከል አንዱ በሆነው የኢትዮጵያ በጎ አድራጎት ህብረት በአሶሳ ከተማ በተገኙበት ምርጫ ጣቢያ ድምጽ አሰጣጥ ሂዴት የምርጫ ቦርድ ህግን በተከተለ መልኩ ሰላማዊ በሆነ መንገድ መካሄዱን ጠቁሟል፡፡

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ዛሬ በተካሄደው በዚሁ 6ኛ ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በክልሉ ውስጥ በሚገኙ በርካታ ወረዳዎች ውስጥ ድምጽ አሰጣጥ ሂደት ተከናውኗል፡፡ በክልሉ በመተከል ዞን አራት ወረዳዎች ውስጥ በሚገኘው 40 በሚደርሱ ምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ በጸጥታ ችግር ምክንያት ዛሬ ድምጽ እንደማይሰጥ የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ ትናንት በአዲስ አበባ ለመገናኛ ብዙሑን በሰጡት መግለጫ አብራርተዋል፡፡

6ኛው ዙር ቀሪና ድጋሚ ምርጫ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአሶሳ ዞንን ጨምሮ በካማሺና መተከል ዞን ወረዳዎች ዛሬ የድምጽ ሲሰጥ ውሏል፡፡ ምርጫው በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልልን ጨምሮ በአፋር ሶማሊና በማዕከላዊ ኢትዩጵያ ክልሎች ዛሬ ምርጫ መካሄዱን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መረጃ ያመለክታል፡፡
ነጋሳ ደሳለኝ
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር