ቤተ-እስራኤላዉያን በእስራኤል | ባህል | DW | 13.12.2012
 1. Inhalt
 2. Navigation
 3. Weitere Inhalte
 4. Metanavigation
 5. Suche
 6. Choose from 30 Languages

ባህል

ቤተ-እስራኤላዉያን በእስራኤል

ቤተ-እስራኤላዉያን ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል በይፋ መሄድ ከጀመሩ ከ 20 ዓመት በላይ ሆኟቸዋል። ግን አመጣጣቸዉና መነሻቸዉ ከየት ይሆን? እነዚህ ከገጠሪቱ ኢትዮጵያ ወደ እስራኤል የገቡት ቤተ- እስራኤላዉያን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? በለቱ ቅንብራችን መነሻቸዉን እና አመጣጣቸዉን በእስራኤልም አኗኗራቸዉን እንቃኛለን ።

የእስያ እና የአፍሪቃ አህጉራት መገናኛ ድልድይ በመባል የምትታወቀዉና በምሥራቃዊዉ የሜዲተራንያን ባህር ዳርቻ ላይ የምትገኘዉ፤ እስራኤል ስምንት ሚሊዮን ግድም ህዝብ እንዳላት ዘገባዎች ያሳያሉ። በአለም ዙርያ ከሚገኙ ከ 120 በላይ አገሮች ዉስጥ ተሰበጣጥረዉ የኖሩ የነበሩ አይሁዳዉያንን ወደ ሀገርዋ በማስገባት ላይ ናት። ከነዚህ ህብረተሰቦች መካከል ከኢትዮጵያ የገቡት ብቸኛዎቹ ጥቁር አፍሪቃዉያን ቤተ-እስራኤላዉያን ናቸዉ። እነዙህ ህዝቦች መነሻቸዉ ከየት ይሆን? በቴላቪብ ዩንቨርስቲ የታሪክ ምሁር የሆኑት ዶክተር አንበሴ ተፈራ ማብራርያ ሰጥረዉናል።

ቤተ -እስራኤላዉያን እትብታቸዉ ከተቀበረበት ሀገር ወጥተዉ ለባህልና ወጉ አዲስ ወደ ሆኑበት ወደ እስራኤል መግባት ከጀመሩ ከ30 ዓመታት በላይ ተቆጥሯል። ምንም እንኳ በእስራኤል ኑሮ የተሟላ ቢሆንም ፤ አብዛኛዎቹ የአኗኗር ስልቱን ባህልና ቋንቋዉንም መላመዱ እንዳሰቡት ቀላል ሆኖ ያገኙት አይመስልም ። ከሁለት ሳምንት ግድም በፊት የእስራኤሉ ወኪላችን ግርማዉ አሻግሪ ራድዮ ጣብያችን በሚገኝበት በጀርመን ቦን ከተማ ለስልጠና ብቅ ባለበት አጋጣሚ፤ እዉነት ቤተ እስራኤላዉያኑ በእስራኤል ችግር ገጥሟቸዋልን ስል ለጠየቅነዉ ሰፋ ያለ መረጃ ሰጥቶናል።

Juden stehen an der Klagemauer in der Altstadt der israelischen Hauptstadt Jerusalem

ከኢትዮጵያ ወደ እስራኤል ከሄዱት አመዛኙ በቤተሰብ፤ በትዳር በርካታ ችግሮች እንደሚያጋጥሟቸዉ፤ ከዝያም በላይ በማህበረሰቡ ዉስጥ አልፎ የተለያዩ ወንጀሎች እንደሚፈፀሙም እና ይህንን ችግር ለመፍታት የተለያዩ ጥረቶች በመደረግ ላይ መሆናቸዉን የእስራኤሉ ወኪላችን ሳይገልጽ አላለፈም። ቤተ-እስራኤላዉያኑ በእስራኤል ዘረኝነት እንዳለ ቢሰማም በመንግስት ደረጃ ይህ ነገር አይታይም ሲሉ፣ ጋዜጠኛ ግርማዉ አሻግሪ እና በቴላቪብ ዩንቨርስቲ የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አንበሴ ገልጸዉልናል። በእስራኤል የሚኖሩ ቤተ እስራኤላዉያን እጅ ለእጅ ተያይዘዉ ከሀገሪዉን ህዝብ ጋር ተቀራርበው ባህሉን ተቀብለው ቢኖሩ ኑሮ እጅግ እንደሚቀላቸዉ ጋዜጠኛ ግርማዉ አሻግሪም ሆነ የታሪክ ምሁሩ ዶክተር አንበሴ ተፈራ ሳይገልጹ ግን አላለፉም። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!

አዜብ ታደሰ

ሂሩት መለሰ

Audios and videos on the topic

 • ቀን 13.12.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/171gW
 • ቀን 13.12.2012
 • አዘጋጅ
 • ያትሙ ገፁን ያትሙ
 • Permalink https://p.dw.com/p/171gW