ቤተ እስራኤላዉያንና የእስራኤል ውሳኔ | ዓለም | DW | 17.07.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ዓለም

ቤተ እስራኤላዉያንና የእስራኤል ውሳኔ

ውሳኔው በአዲስ አበባና በጎንደር ከተማ ተፈናቅለው ወደ እሥራኤል ለመግባት በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቤተ እስራኤላውያን ቤተሰቦችን አስጨንቋል ።

የእስራኤል መንግሥት ከኢትዮጵያ የመጨረሻ ተጓዞች ናቸው ያላቸው በመቶዎች የሚቆጠሩ በጎንደር ከተማ ይጠባበቁ የነበሩ ቤተ እስራኤላውያን ነሐሴ 28 2013 ተጠቃለው እስራኤል እንደሚገቡ አስታውቋል ። ይህ ውሳኔም በአዲስ አበባና በጎንደር ከተማ ተፈናቅለው ወደ እሥራኤል ለመግባት በተስፋ ይጠባበቁ የነበሩ በሺህዎች የሚቆጠሩ የቤተ እስራኤላውያን ቤተሰቦችን አስጨንቋል ። እስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ይሁዲዎችም ውሳኔውን በመቃወም ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል ። ግርማው አሻግሬ ዝርዝሩን አዘጋጅቷል ።

ግርማው አሻግሬ

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic