ቤተ እስራላዊያን ከ25ዓመት በኋላ | ኢትዮጵያ | DW | 25.05.2016
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ቤተ እስራላዊያን ከ25ዓመት በኋላ

የእስራኤል መንግስት > በሚባል ተልዕኮ ከ14,000 በላይ የኢትዮጵያዊያን የሁዲዎችን ወይም በተለምዶ ፋላሻዎችን ወደ ኢስራኤል ከወሰደ በዚሕ ሳምንት 25 ዓመቱን ደፈነ። በጊዜዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ የፖለትካ አለመረጋጋት በመኖሩ የእስራኤል መንግስት የሁዲዎችን ለማዳን ዘመቻዉን ማድረጉብ አስታዉቆ ነበር።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 04:09
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
04:09 ደቂቃ

ቤተ እስራላዊያን

ሁለት ቀን የፈጀዉ ዘመቻ የተደረገዉ የቀድሞዉ አማፂ ቡድን ኢሕአዴግ አዲስ አበባን ከመቆጣጠሩ ከዕለታት በፊት ነበር። ከዘመቻዉ በኋላም በሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን ይሁዲዎች እስራኤል ገብተዋል። ከ25 ዓመት በኋላ አሁን የኢትዮጵያዉያን እስራኤላዉያኑ ኑሮ ምን እንደሚመስል፣ እንዲሁም ስኬቶች እንዳጋጠማቸዉ ፈተናዎች እንዳሉ ቤተ እስራላዊያኑ ይናገራሉ።


ከዘመቻ ሶሎሞን በፊት ወደ እስራኤል የመጡት እና ፣ በእስራኤል በጋዚጤኝነት ሙያ እየሰሩ የምገኙት ቤቴ እስራላዊዉ አቶ አላዛር ራሃሚም ወደ እስራኤል ሲመጡ የነበራቸዉ ስሜት አገሪቱ መንፈሳዊ እና ቅዱስ ቦታ እንደሆች ያስቡ እንደነበር ይናገራሉ። ይሁን እንጅ እስራኤል ካሰቡት በጣም የተለየች መሆኗን እና ከእትዮጵያ ጋር ሲወዳደር ኢትዮጵያ ለምለም የሆነች እና ዛፍ የበዛባት መሆኗን ይናገራሉ። ወደ እስራኤል መምጣቴ የሚቆጨኝ ነገር የለም፤ ድል እንጂ የሚሉት አቶ አላዛር በትምህርትም በስራም ጥሩ ደረጃ ላይ ነኝ ይላሉ። ይሁን እንጅ መንገዱ ለቤቴ እስራላዊያን ቀላል እንዳልሆነ እና ኢሰብአዊ ድርጊቶች እንደሚፈፀሙ ይናገራሉ። መነግስት በመርሕ ደረጃ ዘረኝነት ባይኖረዉም ባሕሉና ወጉ ሊጣጣም እንዳልቻለ እና እሱም ወደ ግጭት እንዳመራ ይናገረሉ።

Israel Tel Aviv Protestaktion äthiopische Juden Ausschreitungen

የኢትዮጵያዊያን የሁዲዎች ተቃዉሞ በቴል አቭቭ


ቤተ እስራላዊያን ሴቶች ልጅ እንዳይወልዱ የሚያደርግ መድሐኒት በድብቅ ተሰጧቸዋል የሚባለዉ ጉዳይ እንደሚያበሳጫቸዉ የሚናገሩት ዶክተሮቹ ወይም ነርሶቹ ሳይሰጣቸዉ በፊት ማስረዳት ነበረባቸዉ ሲሉም አስተያየታቸዉን አቅርበዋል። ቤቴ እስራላዊያንን ለመቀበል የእስራኤል መንግስት አቁማለች የምባለዉ ትክክለኛ መረጃ አይደልም የምሉት አቶ አላዛር ጉዳዩን በቅርብ እንደምያዉቁ እና በቅርብም ለዘገባ እንደሄዱ ይናገራሉ። ኢትዮጲያ የቀሩት ቤተ እስራላኤላዉያኑ ስራ በቀላሉ እንደማያገኙ እና ከዉጭ ያሉ ዘመዶቻቸዉ ገንዘብ እንደሚጠብቁም ይናገራሉ።

Bete Israelis in Gondar

ቤቴ እስራላዊያን በጎንደር


በዚህ ጉዳይ ላይ በዶቼ ቬሌ የፌስቡክ ገፅ ዉይይት ተደርጎ ነበር። ተሳታፊዎቹ እንደሚሉት ቤተ እስራላዉያኑ ወደ እስራኤል እንዳይሔዱ በደርግ ጊዜ ተከልክለዉ እንደነበር፣ እና ከዛ በኋላ መጓዛቸዉና በእስራኤል ጥሩ ኑሮ ኢየኖሩ እንደምገኙ አስተያያታቸዉን ሰተዋል።

መርጋ ዮናስ

ነጋሽ መሓመድ

Audios and videos on the topic