1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ከኢኮኖሚው ማሻሻያው ወዲህ የዶላር ይዞታ

ሥዩም ጌቱ
ረቡዕ፣ መስከረም 15 2017

በገቢ ንግድ ላይ የተሰማሩ አስተያየት ሰጪ እንደሚሉት ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ የውጪ ምንዛሪን ለነጻ ገቢያ ስርዓት ከተተወ ወዲህ የባንኮች የውጪ ምንዛሪ ክምችት ከፍ በማለቱ የምንዛሪው አሰጣጥ ስርዓቱ ባይቀየርም የተሻለ የዶላር መጠን ለአስመጭዎች እንደሚሰጥ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4l4MQ
Währung | Euro, Yuan und Dollar
ምስል Antonio Pisacreta/ROPI/picture-alliance

ለገቢ ንግድ የዉጭ ምንዛሪ አሰጣጥ ስርዓት

ኢትዮጵያ የውጪ ምንዛሪ ማሻሻያ ካካሄደች ከወራት ወዲህ የባንኮች የውጪ ምንዛሪ ክምችት አቅምም ከፍ ማለቱ ተዘግቧል ። ከምንም በላይ ግን ሰላም የራሱ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው በባለሞያ ተገልጧል ። የባንኮች የዶላር ምንዛሪ መጠን ከትይዩ ገበያ ጋር በአንጻራዊነት እየጠበበ በመጣበት ባሁኑ ወቅት ለአስመጪዎች የሚሰጥ ዶላር መጠነኛ መሻሻል ማሳየቱ ተጠቅሷል ። የዶላር  አሰጣጥ ስርዓቱ ላይ ግን ለውጥ አለመኖሩ እየተነገረ ነው የሚነገረው ። 

ለገቢ ንግድ የዉጭ ምንዛሪ አሰጣጥ ስርዓት

በገቢ ንግድ ላይ የተሰማሩ አስተያየት ሰጪ እንደሚሉት ኢትዮጵያ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ በማድረግ የውጪ ምንዛሪን ለነጻ ገቢያ ስርዓት ከተተወ ወዲህ የባንኮች የውጪ ምንዛሪ ክምችት ከፍ በማለቱ የምንዛሪው አሰጣጥ ስርዓቱ ባይቀየርም የተሻለ የዶላር መጠን ለአስመጭዎች እንደሚሰጥ ለዶቼ ቬለ በሰጡት አስተያየት አረጋግጠዋል፡፡

በአንድ የግል ባንክ ውስጥ በውጪ ምንዛሪ ጉዳዮች ክፍል ውስጥ የሚሰሩና ማንነታቸውን ግን ከመግለጽ የተቆጠቡት አስተያየት ሰጪ ደግሞ ከኢኮኖሚው ማሻሻያ ወዲህ እሳቸው የሚሰሩበት ባንክን ጨምሮ የባንኮች የውጪ ምንዛሪ ክምችት አቅም በጉልህ መጨመሩን አረጋግጠውልናል፡፡ ይህም ባንኮች ለአስመጪዎች የውጪ ምንዛሪ ፍላጎትን የመስጠት (የማቅረብ) አቅማቸውን ከፍ ቢያደርግም በአሰጣጥ ስርዓቱ ላይ ግን ከከዚህ ቀደሙ የተሻሻለ ፖሊሲ አለመውጣቱን አስረድተዋል፡፡

አዲስ ,ab,ባ ከተማ፤ ብሔራዊቴአትር አካባቢ
በአዲስ አበባ ከተማ ብሔራዊ ቴአትር አካባቢ በሚገኝ መደብር የውጭ መገበያያ ገንዘቦች የሚመነዝሩ ነጋዴ ሥራው “እንደ ወትሮው አይደለም” ሲሉ ቀደም ሲል ለዶይቼ ቬለ ተናግረው ነበር።ምስል Eshete Bekele/DW

“እንደከዚህ ቀደሙ በባንኩ የገቢ ንግድ ሂደት እንደ ንግድ ፍቃዱ ይዞታ ለንግድ በአንዴ የሚፈቀደው እስከ 10 ሺህ ዶላር ነውና የውጪ ምንዛሪ ግብይት ላይ ከከዚህ ቀደሙ ምንም ለውጥ አልተስተዋለም” ያሉት አስተያየት ሰጪው የባንክ ባለሙያ የውጪ ምንዛሪ ክምችት ግን ከሪፎርሙ ወዲህ በጉልህ መጨመሩን አልሸሸጉም፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከኢኮኖሚው ማሻሻያ ወዲህ በተለያዩ ጊዜያት የውጪ ምንዛሪ ክምችት አቅምን የሚያሳድጉ አሰራሮችን እያወጣሁ ነው ሲል ተስተውሏል፡፡ የባንኮች የውጪ ምንዛሪ ግብይት ከትይዩ ገቢያ ጋር ያለው ልዩነትም በአንጻራዊነት በእጅጉ እየጠበበ መጥቷል፡፡ ባንኮች ለአነብነትም አንድ የአሜሪካን ዶላርን በብር የሚገዙበት የምንዛሪ መጠን ከ57 ብር በመነሳት ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በእጥፍ አድጎ ወደ 112 ብር ከፍ ብሎ እየተመነዘረ ነው፡፡ ይህም ከትይዩ የውጪ ምንዛሪ ገቢያ ጋር ሲነጻጸር እጥፍ የነበረው የባንኮች የምንዛሪ ዋጋን ወደ አነስተኛ ልዩነት ዝቅ አድርጎታል፡፡ በተለይም በቅርቡ ባንኮች «ካሽጎ» በሚል የሃዋላ አገልግሎት አንዱን የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር በመመንዘር የዶላር ክምችት አቅማቸውን በውል እያሳደጉ መሆኑም ተነግሯል፡፡

ባንኮች አንድ የአሜሪካን ዶላርን በብር የሚገዙበት የምንዛሪ መጠን ከ57 ብር በመነሳት ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በእጥፍ አድጎ ወደ 112 ብር ከፍ ብሎ እየተመነዘረ ነው፡፡
ንኮች ለአነብነትም አንድ የአሜሪካን ዶላርን በብር የሚገዙበት የምንዛሪ መጠን ከ57 ብር በመነሳት ባለፉት ጥቂት ወራት ብቻ በእጥፍ አድጎ ወደ 112 ብር ከፍ ብሎ እየተመነዘረ ነው፡፡ ምስል MICHELE SPATARI/AFP

የውጪ ምንዛሪ ነጻ ገቢያና ዘለቄታዊነቱ 

የኢትዮጵያ መንግስት  ከወራት በፊት ያደረገው የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፖሊሲ አንዱና ዋነኛው ግብ የወጪ ንግድን በማበረታታት የውጪ ምንዛሪ አቅምን ማላቅ ነው የሚሉት የምጣነ ሃብት ባለሙያ ዶ/ር አጥላው ዓለሙ፤ የማሻሻያውን ዘለቀታዊ ግብ ለመገምገም ግን የበለጠ ጊዜ ያስፈልገዋል ነው ብለዋል፡፡ “እንደተጠበቀው የብር ዋጋ እንዲቀንስ እና የዶላር ዋጋ እንዲጨምር ያደረገው የነጻ ገቢ ምንዛሪው ጅማሮ የዶላር ክምችቱን አቅም ከፍ አድርጎታል” ብለዋል፡፡

የምጣኔ ሃብቱ ባለሙያ ዶ/ር አትላው አክለው እንዳሉት ግን ለኢኮኖሚ ማሻሻያው ዘላቂ ግብ እውን መሆን ዘለታዊ መፍትሄ ያሻዋል፡፡ “ትልቁ ስራ መሰራት ያለበት የውጪ ንግድን ማበረታታት ላይ ነው” የሚሉት ባለሙያው ለዚህ ደግሞ የማምረት እና የምርታማነት (ተወዳዳሪ የምርት ጥራት) ላይ አተኩሮ መሥራት ነው ብለዋል፡፡

ሥዩም ጌቱ
ታምራት ዺንሳ
ማንተጋፍቶት ስለሺ