ባራክ ኦባማ በአውሮጳ | አውሮጳ/ጀርመን | DW | 30.03.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አውሮጳ/ጀርመን

ባራክ ኦባማ በአውሮጳ

በመጪው ታህሳስ በኮፐንሀገን ዴንማርክ ከሚካሄደው የዓለም የአየር ንብረት ጉባኤ አንፃር አሜሪካ አንዳች ቆራጥ አቋም ስለመውሰዷ ብዙዎች ከወዲሁ ማወቅ ይፈልጋሉ። የአየር ንብረት ጉዳይን አስመልክቶ በኦባማ የፕራግ ጉብኝት ዩናይትድ ስቴትስና የአውሮጳ ህብረት የሚወያዩበት ጉዳይም ይሆናል።

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ

ብሪታንያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ የቼክ ሬፑብሊክ እና ቱርክ፤ የየዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ከነገ ጀምሮ የሚጎበኟቸው የአውሮጳ ሀገሮች ይሆናሉ። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ዋና ዓላማም፤ በለንደን በሚካሄደው የቡድን ሃያ ጉባኤ እንዲሁም በሽትራውስበርግ እና በኬህል ከተሞች በሚከናወነው የሰሜን አትላንቲክ ቃል-ኪዳን ድርጅት ስብሰባ ላይ ለመካፈል እንደሆነም ታውቋል። ከወዲሁ የአውሮጳ ሕዝብና ፖለቲከኞች የፕሬዚዳንቱን ጉብኝት በከፍተኛ ጉጉት እየጠበቁት ነው። በተለይ የአውሮጳ ፖለቲከኞች ኦባማ በርግጥም የሚስማሟቸው ስለመሆኑ ከጉብኝቱ ማረጋገጥ ይፈልጋሉ። ሆኖም አንዳንድ ተንታኞች ያን ያህል በከፍተኛው መጠበቅ እንደማይገባ እያስጠነቀቁ ነው።

ማንተጋፍቶት ስለሺ