ባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ | ባህል | DW | 22.04.2009
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሲቓቓም ያኔ በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ-መንግስት መጋዘን የነበረ ቤትን ወደ አዳራሽነት በመቀየር ነበር። በወቅቱ በሀገሪቱ የነበሩ የኪነ-ጥበብ ተቓማት ከቁጥር የማይገቡ ስለነበር፤ የባህል ማዕከሉ መቓቓም፤ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብንና ከዩኒቨርሲቲው ውጭ የሚገኘውን ህብረተሰብ ከጥበብ ማዕድ ተቓዳሽ ለማድረግ በማለም ነበር።

ጥበብ ፋይዳው ላቅ ያለ ነው

ጥበብ ፋይዳው ላቅ ያለ ነው

ባለፈው ሳምንት፤ ጀርመን አገር፣ ሀምቡርግ ከተማ ውስጥ ስለሚገኘውና “የፈረስ ጋጣ ባህል ማዕከል” ስለሚባለው አንድ የባህል ማዕከል ማንሳታችን ይታወሳል። ዛሬ ደግሞ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ የአገሪቱን ባህልና ጥበብ ከማበልፀግ አንፃር ምን ሚና እየተጫወቱ ይገኛሉ የሚለው ነጥብ ላይ እናተኩራለን። የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከልም ማንጸሪያችን ይሆናል። ቀድሞ በዚህ የባህል ማዕከል ሲንቀሳቀሱ ከነበሩ የጥበብ ሰዎች መካከል አንዱ የሆነው አርቲስት ሸዋፈራሁ ደሳለኝና አርቲስት ገረመው አሰፋ የሚሉን ይኖራቸዋል።