ባህልን ማወቅ ለልማት | ባህል | DW | 06.01.2011
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ባህልን ማወቅ ለልማት

በአለማችን ልማትን ለማስፋፋት እና የሰዉን አዕምሮ ለማበልጸግ በቅድምያ የህብረተሰብን አስተሳሰብ ሰነ-ልቦናዊ አቋም፣ ሃይማኖት አገረሰባዊ ልማድ፣ በአጠቃላይ ባህሉን ማወቅ ተቀዳሚ ተግባር መሆኑን ምሁራን ይገልጻሉ።

default

ከባህል ጥናት ዉጭ ልማትን ማምጣት አይቻልም በሚል ምሁራን በተቀዳሚ የህብረተሰብን ባህል በማጥናት የአካባቢ የአገር አቀፍ ከዝያም ባለፈ አለም አቀፍ ልማትን ለመዘርጋት እንደሚቻል ይገልጻሉ። በአለማችን ላይ የባህልን በአጠቃላይ የፎክለርን ጥናት በአግባቡ የጀመሩት በ 18 ኛዉ ክፍለ ዘመን መጨረሻ ላይ የኖሩት ጀርመናዉያኑ ወንድማቾች ዊልያም እና ያኮብ ግሪም ናቸዉ። እንደ ምሁራን ገለጻም በባህል ጥናት ዘርፍ ፊላንዳዉያን የመቶ አመት ታሪክን በመያዝ ተቀዳሚዉን ቦታ መያዛቸዉን ይገልጻሉ። በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በፎክሎር ጥናት እ.ኢ 1999 አ.ም በመጀመርያ ዲግሪ በ1995 በመቀጠል ለማስተርስ ዲግሪ እንዲሁም ከባለፈዉ አመት ጀምሮ የፎክሎር ትምህርት ጥናት ይሰጣል። ለልማት በባህል የቋንቋ መስተጋብር ባለሞያ አቶ ሃይለየሱስ ባላ በአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ በዚሁ የባህል ትምህርት አኳያ በጥናት ላይ ይገኛሉ። የለቱ እንግዳችን ናቸዉ ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ