ባህላዊ፣ የፍቅር ዜማ | ባህል | DW | 13.03.2008
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ባህላዊ፣ የፍቅር ዜማ

አረ መዉደድ መዉደድ፣ መዉደድ አባዳንዴ፣ አይወጋ በጦር አይሞት በጎራዴ፣ ዳኛ አይመረምረዉ ሃኪም አያድነዉ፣ ከፈጣሪ በታች ሃይለኛዉ ፍቅር ነዉ። ስለፍቅር ዘፈን ልናነሳ እንደተነሳን የገመታችሁ ይመስለናል በፍቅር ግዜ በዜማ የሚገጠሙትን ግጥሞች አሰባስበን ባለሞያ አነጋገርን ስለለፍቅር ግጥሞች ልንጠቃቅስ መርጠናል።

default

ዘፈን፣ የሰዉ ልጅ በኑሮዉ ዉስጥ ያለበትን ችግር ለመፍታት የሚጠቀምበት ዘዴ ነዉ ሲሉ ምሁራን ይገልጻሉ። በአገራችን በተለይ በገጠሩ አካባቢ የስልጣኔዉን አለም እንብዛም የማያዉቀዉ፣ ዘፈንን በአዕምሮዉ ጠይቆ ሊመልሳቸዉ ያልቻላቸዉን ነገሮች በማንጎራጎር በዘፈን ፍች ሊሰጥባቸዉ ይሞክራል። ለምሳሌ የጨለማ የቀን መፈራረቅ የተራራ መብዛት፣ በቅሎ የሴት ተፈጥሮ ኖርዋት አለመዉለድዋ የመሳሰሉት ጥያቄዎችን መልስ ለመስጠት ይገጥማል አስፈሪ የሆነ ነግርም ካለ በንጉርጉሮ፣ በዜማ እንደሚወጣ ጽሁፎች ይገልጻሉ። የህብረተሰብ ጥናት አዋቂዉ አቶ መስፍን መሰለ ስለፍቅር ዘፈኖች ያጫዉቱናል መልካም ቆይታ።