ባህላዊ የገና በአል አከባበር | ባህል | DW | 05.01.2012
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ባህላዊ የገና በአል አከባበር

በአገራችን የገና በአል የበአላት ሁሉ በኩር ትልቅ የምስራች ያለበት በአል በመባል በደማቅ ይከበራል። በባህላችን በገና በአል እንደ አቅማችን ዳቦ ደፍተን ጠላ ጠምቀን ንጹህ ለብሰን የገናን በአል ከቤተሰብ ተሰባስበን እናከብራለን።

default

ጀርመናዉያን የዛሬ ሁለት ሳምንት ግድም በደማቅ ያከበሩት የገና በአል፣ ኢትዮጵያዉያን ባልንጀሮቻቸዉ ለገናን በአል ጋብዘዋቸዉ ካከበሩ የገናን በአል ለሁለተኛ ግዜ ከኢትዮጽያን ጋር እልላከበሩ በመግለጽ ስለ ኢትዮጽያ ባህል ያወሳሉ። እንደ አገራችን እዚህ በጀርመን እንስራ ሳይኖር ቀርቶ ለገና በአል የተጠመቀ ጠላ ባይጠጣም፤ ዳቦ ዶሮ በኢትዮጽያዊ ባህል ተጠምቆ እና ተሰርቶ በደማቅ ይከበራል። በኢትዮጵያ አብያተ-ክርስትያናትም እንዲሁ በአሉን በማስመልከት የቅዳሴ ስርአት ይኖራል፤ በኢትዮጵያ አርባ ቀን ተጽሞ ገና ወይም ልደተ ክርስቶስ ሲከበ የአከባበሩ ሁኔታ እንደ አካባቢዉ የተለያየ መሆኑን መላከ ምክር ከፍያለዉ መራኒ እና አቶ አበረ አዳሙ ይነግሩናል። ሙሉዉን ቅንብር ያድምጡ!


አዜብ ታደሰ

ተክሌ የኋላ

Audios and videos on the topic