ባህላዊ ሙዚቃ በጃዝ እና ሶል | ባህል | DW | 19.12.2013
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ባህል

ባህላዊ ሙዚቃ በጃዝ እና ሶል

ለሶስት አስርተ ዓመታት ከመድረክ ርቆ ቆይቶ፤በቅርቡ እጅግ አስደናቂ የተባሉትን እንብሮቹን ይዞዳግም ብቅብሎአል። በ1970ዎቹ ታዋቂ በነበረው ዋሊያስ ባንድ ውስጥ በጃዝ እና በሶልስልት የተቀነባበረ ሙዚቃን በመጫወት ዕውቅናን ያገኘው ኃይሉ መርጊያ።

Logo ENJOY JAZZ

በዩናትድ ስቴትስ ዋሽንግተን የሚኖረዉ የረቂቅ ሙዚቃ ቅንብር ባለሞያዉ ኃይሉ መርጊያ ኢትዮጵያዊ ቅላፂ የተላበሰ የጃዝ ሙዚቃ ቅንብሩን ከሁለት የኦስትርያ የጃዝ ሙዚቃ ባልደረቦቹ ጋር በመሆን በተለያዩ የአዉሮጳ ሀገራት አቅርቦ በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን አስደምሞአል። ሙዚቀኛ ሃይሉ መርግያ ጀርመን በሚገኙ ሁለት ከተሞች የጃዝ ድግሱን ሲያቀርብ ተገኝተን፤ በዕለቱ ዝግጅት ከሙዚቃዉ ድግስ በጥቂቱ ልንላችሁ ይዘናል፤ በኢትዮጵያ የጃዝ ሙዚቃ ወርቅማዎቹ ግዝያት በሚባልበት በ1960 ዎቹ እና 70 ዎቹ ከዋልያስ ባንድ ጋር ብቅ ያለዉ ኃይሉ መርጊያ በተለያዩ የሙዚቃ መሣርያ የተቀነባበሩ የኢትዮጵያ ባህላዊ ሙዚቃዎችን የተላበሰዉን ሥራዎቹን ከጃዝ ጋር በማጣመር ይዞልን ይቀርባል የሚል ነበር፤ኃይሉ መርግያ በጀርመኑ መድረክ ሊቀርብ ከጥቂት ቀናት በፊት በድረ-ገጾች ላይ የተለቀቀዉ የግብዣ ጥሪ።

ሙዚቀኛ ኃይሉ መርጊያ የጃዝ ድግሱን ለማሳየት ወደ አዉሮጳ መምጣት፤በርካታ ሙዚቀኛ አፍቃሪ የሰማ አይመስልም በተለይ በተለይ ኢትዮጵያዊዉ፤እንድያም ሆኖ የጃዝ ድግሱ በቀረበበት በበርሊን እና በዲስልዶርፍ ከተማ በተዘጋጀዉ አነስተኛ መድረክ በርካታ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን አስፈንጥዞአል፤አስደንሶአል፤ኢትዮጵያዉያኑንም እንዲሁ ወደ ጥንቱ ወደ ሰባዎቹ ዓመታት በትዝታ አስኮብልሎ፤አስጨፍሮአል። እንደ ሙዚቀኛ ኃይሉ«እንዲህ ሀገር ለሀገር ሙዚቃ ድግስን የማቅረብ ልምድ ስላልነበረን ነዉ እንጂ ቀደም ብለን በደንብ ተዘጋጅተን ቢሆን ኖሮ በበርካታ ከተሞች ድግሳችንን እናሳይ ነበር» ሲል በቁጭት ተናግሯል፤ታዳሚዉም ቢሆን እንዲህ የጥንት አይነት ሙዚቃን መዉደዱእጅግ አስደስቶኛል ሲል ላቀረበዉ የሙዚቃ ድምቀት የሰጡትን ታዳሚዎች አወድሶአል። የ67 ዓመቱ ኃይሉ መርጊያ ሙዚቃን እንዴት ጀመረ፤ከሙዚቃ ድግሱ በኃላ በሰጠን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ገና በአስራ አራት ዓመቱ መጀመሩን እና፤ አሁን ከሃያ መታት ግድም በኃላ እንደገና ወደ መድረክ ብቅ ማለቱን ተናግሮአል። ኃይሉ መርጊያ ከዋልያስ ባንድ ጋር ኢትዮጵያን ለቆ ከወጣ ሰላሳ ዓመታት እንደሆነዉም ተናግሮአል። ለረጅም ዓመታት እዚህ በጀርመን በኮለኝ ከተማነ ዋሪ የሆኑት አቶ ተወልደ፤ በኃይሉ መርጊያ የሙዚቃ ድግስ ለረጅም ዓመት የተለዩዋትን ኢትዮጵያን፤ ከዝያም የጥንቱን ትዝታ ቀስቅሶባቸዉ ለደስታቸዉ መግለጫ ቃላት አጥሮአቸዉ ነበር። ኃይሉ መርግያ ትክክለኛ መድረክን ቢያገኝ በዓለማችን ዝናን ካተረፉት ታዋቂ የረ ቂቅ ሙዚቀኞች አይተናነስም ሲሉ በሙዚቃዉ መርካታቸዉን ገልፀዋል።

ሌላዉ በኮለኝ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የዚሁ የጃዝ ሙዚቃ ድግስ እድምተኛ አቶ ተክሌ አዳሃኖም በቀድሞ ግዜ የኃይሉ መርጊያ የስራ ባልደረባ ነበሩ፤ ከሙዚቃዉ ዓለም እና ከኃይሉ ጋር ከተለያየን ዘመናትን ብናስቆጥርም ሙዚቃ የዓለም ቋንቋ ነዉና መልሰን ተገናኘን ብለዋል። አቶ ተክሌ አዳሃኖም፤ የኤርትራ ተወላጅ መሆናቸዉንና ከሰላሳ ዓመት በፊት ከኃይሉ መርጊያ ጋር በአዲስ አበባ በተለያዩ ታዋቂ ቡና ቤቶች እና ሆቴሎች የሙዚቃ ድግስን ያቀርቡ እንደነበር ተናግረዋል። ሙዚቀኛ ኃይሉ መርጊያ ከሙዚቃ ስራዎቻቸዉ በኢትዮጵያዉ የሙዚቃ መድረክ እንደሚገኙም ተናግረዋል። ሙሉ ቅንብሩን የድምፅ ማድመጫዉን በመጫን ያድምጡ።

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሃመድ

Audios and videos on the topic