ቢቢሲ ባንድ ኤይድን ይቅርታ መጠየቁ | ኢትዮጵያ | DW | 04.11.2010
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

ኢትዮጵያ

ቢቢሲ ባንድ ኤይድን ይቅርታ መጠየቁ

ባንድ ኤይድ የተባለው የዕርዳታ ድርጅት ለ 1977 ቱ የኢትዮጵያ ረሀብ መርጃ ያሰባሰበው በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ በህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ ለጦር መሣሪያ መግዣ ውሏል ሲል የብሪታኒያ ዜና መሰራጫ ኮርፖሬሽን ቢቢሲ ባለፈው ዓመት ላሰራጨው ዘገባ ዛሬ ይቅርታ ጠየቀ ።

default

ቦብ ጌልዶፍ

ቢቢሲ ዛሬ ባወጣው መግለጫ በዘገባው ምክንያት ስለ ድርጅቱ የተሳሳተ ግንዛቤ በመፈጠሩ ጥፋተኛ መሆኑን አስታውቋል ። የህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የቀድሞው ከፍተኛ የአመራር አባልና በወቅቱ የድርጅቱ ወታደራዊ ክፍል ሀላፊ የነበሩት ዶክተር አረጋዊ በርሄ የቢቢሲ ይቅርታ አስገራሚ ነው ይላሉ ።

ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ