ቡርኪናፋሶ፦ ወጣት የሥነቴክኒክ ጠበብት | አፍሪቃ | DW | 07.10.2015
  1. Inhalt
  2. Navigation
  3. Weitere Inhalte
  4. Metanavigation
  5. Suche
  6. Choose from 30 Languages

አፍሪቃ

ቡርኪናፋሶ፦ ወጣት የሥነቴክኒክ ጠበብት

«አፍሪቃ በእንቅስቃሴ ላይ» በተሰኘው ልዩ ዝግጅት በእግረ-ኅሊና ወደ ቡርኪናፋሶ እናቅና። እዚያም በስነ-ቴክኒክ እመርታ በመታገዝ በአፍሪቃ ማኅበራዊ ለውጥ ለማምጣት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ለማበርከት ድርጅት ያቋቋሙ ለኮምፒውተር ልዩ ፍቅር ያላቸው ወጣቶችን ይገኛሉ።

አውዲዮውን ያዳምጡ። 03:58
አሁን በቀጥታ እየተሰራጨ ያለ
03:58 ደቂቃ

ወጣት የሥነቴክኒክ ጠበብት

ኦዋጋ የተሰኘውን ቤተ-ሙከራቸውን ካቋቋሙት ወጣቶች መካከል አንደኛው ጂላድ ዡዌላ በጽ/ቤታቸው በር ላይ ከውጭ በኩል የድርጅታቸው መለያ ባንዲራቸውን እየሰቀለ ነው። ገንዘብ ለመሰብሰብ ሕዝብን የማስተባበር ስልት ምስጋና ይግባውና ለመረጃ ቴክኖሎጂ ድርጅታቸው ማቋቋሚያ የሚኾን ገንዘብ ማሰባሰብ ችለዋል። አኹን የሚፈልጉት ሰዎች ማን እንደኾኑ እንዲያውቋቸው ነው።

"ሰዎች እዚህ ኦጋዱጉ ውስጥ በቅጡ እንደማያውቁን መቀበል አለብኝ። በድረ-ገጻችን የተነሳ ብዙ ሰዎች ስለ እኛ የሚያውቁት ከሀገር ውጪ፤ በተለይ አውሮጳ ውስጥ ነው። ያ እንዲለወጥ ግን እዚህ ዋጋዱጉ ውስጥ ባለን ቤተ-ሙከራችን ጥረት እያደረግን ነው።"

በሦስት አቅጣጫ ማለትም 3-D የሚታይ ዲጂታል ኅትመት ቤተ-ሙከራ፦ በኮምፒውተሮች እገዛ በቀላሉ ሊንቀሳቀሱ በሚችሉ ማናቸውንም ነገሮች ዕውን ለማድረግ በሚያስችሉ መሣሪያዎች የተዋቀረ አነስተኛ የሥራ ማደራጂያ ቦታ ነው።በሦስት አቅጣጫ ማለትም 3-D የሚታይ ዲጂታል ኅትመት መሣሪያ ቤተ-ሙከራ ውስጥ የሚያሰማው ድምጽ ነው። ጂላድ ማተሚያውን ያገኘዉ ፈረንሣይ ውስጥ በተደረገ የኮምፒውተር ውድድር ላይ ተካፍሎ ተሸልሞ ነው። ማተሚያዉ የኩራቱ እና የደስታው ምንጭ ነው። አኹን በዚህ ማተሚያ ታግዘው በተለያየ መንገድ አካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ምትክ የሰውነት ክፍል ቁሶችን ከሚያመርቱ በአካባቢው ከሚገኙ ባለሙያዎች ጋር ለመሥራት ተስፋ ሰንቀዋል።

"ምትክ የሰውነት ክፍል ቁሶችን የሚያመርቱት ባለሙያዎች በሦስት አቅጣጫ የሚታይ ዲጂታል ኅትመት ይቅርና ማተሚያውን እንኳን አይተው አያውቁም። ኾኖም በሦስት አቅጣጫ የሚያሳይ ዲጂታል ማተሚያ ምን እንደሆነ እና በሱም ምን ማድረግ እንደሚቻል ሐሳቡ አላቸው።"

የአካባቢው ባለሙያዎች ተተኪ እግሮች እና እጆችን የሚሰሩት እጅግ አድካሚ በሆነ መንገድ በእጃቸው እየታገዙ ነው። አጹ አዶቴ በዚህ አዲስ ስነ-ቴክኒክ ሥራቸው ይቀልልኛል ብለው ከሚያስቡ ባለሙያዎች አንዱ ናቸው።

"ሲመስለኝ በሦስት አቅጣጫ በሚያሳይ ዲጂታል ማተሚያ በመታገዝ በቅርቡ ዐሥር ምትክ የሰውነት ክፍል ቁሶችን በቅጽበት ማምረት ትችላለኽ።"

ቤተ-ሙከራው ለአካባቢው ባለሙያዎች ተግባራዊ እገዛ ከማድረጉም ባሻገር በአንደኛ ደረጃ ትምኅርት ቤቶች የኮምፒውተር ትምኅርቶችን መስጠትን ጨምሮ የተለያዩ የአፈፃጸም ዕቅዶች ላይ ተሳታፊ ነው። ዛሬ ጂላድ በተደጋጋሚ ሲጎበኘው ወደሰነበተው ትምኅርት ቤት ያቀናል።

"ስለኮምፒውተሮች ምን ያኽል እንደምታውቁ አብረን እንመለከታለን። ስለኮምፒውተር አሠራር ቀደም ሲል ግንዛቤው ያላችሁ የበለጠ ዕውቀትን ትገበያላችሁ፤ ስለ መረጃ ስነ-ቴክኒክ አንዳችም ዕውቀቱ የሌላችሁ ደግሞ ዛሬ ፍጹም አዲሱ ዓለም ላይ አንዳች አሠሣ ታደርጋላችሁ።"አብዛኞቹ ልጆች በሕይወታቸው ኮምፒውተር አይተው ስለማያውቁ ጂላድ የሚነግራቸው እና የሚያሳያቸው ነገር እጅጉን አጓጎቷቸዋል።

ልጆቹ ኮምፒውተር እንዴት እንደሚሠራ ግንዛቤ ጨብጠዋል። በጂላድ ርዳታም ከአሮጌ ኮምፒውተሮች ቁሳቁሶችን በመሰብሰብ አዲስ ኮምፒውተር ገጣጥመው አዋቅረዋል። ልጆቹ እና ልጃገረዶቹ በጉጉት ተውጠው ሥራቸው ላይ ተጠምደዋል። ሌሎች ደግሞ የኮምፒውተሩ ቁሳቁሶች ሲገጣጠሙ ከጎን ሆነው እየተመለከቱ ነው። እንግዲህ ልጆቹ ከመረጃ ስነ-ቴክኒክ ባለሙያ ጋር በአንድነት ወደ ኦዋጋ ቤተ-ሙከራ ያቀናሉ። እዚያ አዲስ የተገጣጠመው ኮምፒውተርን ለመሞከር የሚያስችል የኤሌክትሪክ አቅርቦት ይገኛል።

"እያንዳንዱ ልጅ ገና በለጋ ዕድሜው ከኮምፒውተር ጋር ተዋውቆ በዲጂታሉ ዓለም ባዳ እንዳይኾን ዕድሉን መስጠት እንሻለን። ያን ለማድረግም ቤተ-ሙከራችንን እንጠቀማለን። መጠነኛ ዕውቀታችንንም ማስተላለፍ እንፈልጋለን።"

ሁሉም ነገር የመረጃ ስነ-ቴክኒክ ባለሙያው እንዳቀደው የሚከናወን ከኾነ፤ አንደኛ ደረጃ ትምኅርት ቤቱ የራሱ የኾነ የተደራጀ የኮምፒዉተር ክፍል ይኖረዋል።

ፍሎረስ ሔኮ /ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ

Audios and videos on the topic